Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 የዕውቀቴ ወገኔ ቅድመ መደበኛ ፣ አንደኛ ደረጃ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
  • Address አዲስ ከተማ / ክ/ከ/ወረዳ 12 የዕውቀቴ ወገኔ ቅድመ መደበኛ ፣ አንደኛ ደረጃ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ከአጠና ተራ ወደ አስራ ስምንት በሚወስደው መንገድ 18 አደባባይ ሳይሻገር ድልድዩ ስር ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-2-73-90-66
  • Website
  • Deadline30 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-01-30 00:00:00
  • Categories Construction Works

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 የዕውቀቴ ወገኔ ቅድመ መደበኛ ፣ አንደኛ ደረጃ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 ዓ.ም የሰራተኞች የሻይ ክበብ እና ለቢሮ የሚሆኑ ክፍሎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 የዕውቀቴ ወገኔ ቅድመ መደበኛ ፣ አንደኛ ደረጃ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት


የጨረታ መለያ ቁጥር 002/2018 ዓ.ም

 

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 የዕውቀቴ ወገኔ ቅድመ መደበኛ ፣ አንደኛ ደረጃ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በ2018 ዓ.ም የሰራተኞች የሻይ ክበብ እና ለቢሮ የሚሆኑ ክፍሎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

1.     ሎት1. /ለመሰረተ ልማት እድሳትና ጥገና/ የወጪ መደብ 6244 የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ 2% ብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/

2.     ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር /supplier list/ ውስጥ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ በባለስልጣኑ በመንግስት አካል የተሰጠ የምስከር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው

3.     ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው እንዲሁም የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው

4.     የእሴት ታክስ (ቫት) ሰርተፍኬት እና የታክስ ከፋይነት ቲን ቁጥር ሊኖራቸው ይገባል፡፡

5.     ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር 1000190858627 በመክፈል የባንክ ደረሰኝ ይዘው ዘወትር በስራ ሰዓት አዲስ ከተማ / ክ/ከ/ወረዳ 12 የዕውቀቴ ወገኔ ቅድመ መደበኛ ፣ አንደኛ ደረጃ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ከአጠና ተራ ወደ አስራ ስምንት በሚወስደው መንገድ 18 አደባባይ ሳይሻገር ድልድዩ ስር ይገኛል የዕውቀቴ ወገኔ ቅድመ መደበኛ ፣ አንደኛ ደረጃ እና መካካለኛ ደረጃ ት/ቤት ቢሮ ቁጥር 5 ክፍያና /ሂ አስተዳደር ቢሮ ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 (አስር) የስራ ቀናት ከጥዋቱ 2፡30-11:30 ከምሳ ሰዓት ውጪ ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡

6.     ተጫራቾች አንዱ በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ሌላው መስጠት አይችልም፡፡

7.     ተወዳዳሪዎች የሚያቀርቡትን ሰነድ ዋናውን (ፋይናንሻል) እና ፎቶ ኮፒውን (ቴክኒካል) ሰነዶችን ለየብቻ በፖስታ በማሸግ ከላይ በተጠቀሰዉ አድራሻ ወይም ቢሮ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

8.     ጨረታው የሚከፈተው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸዉ በተገኙበት በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 /ሰዓት/ ታሽጎ በእለቱ ከረፋዱ 4፡30 ይከፈታል በአስራ አንደኛው ቀን ምንም አይነት የጨረታ ሰነድ የማንቀበል ይሆናል፡፡

9.     የሚቀርበው የማወዳደሪያ ሀሳብ ላይ የድርጅቱ ኃላፊ ስምና ፊርማ የድርጅቱ አድራሻ እና ስልክ ቁጥር መኖር አለበት፡፡

10. ለአሸናፊ ተጫራቾች በሰነዱ ውስጥ የተመለከተውን ጊዜ ገደብ ውስጥ ማለትም እስከ 7 ቀን ድረስ ቀርበው የውል ማስከበሪያ ያሸነፉበትን የግንባታ ስራ ዋጋ 10% ገቢ አድርገው ውል መዋዋል አለባቸው።

11. መስሪያቤቱ ተገቢ ነው ብሎ ካመነበት ከጨረታው አሸናፊ ድርጅት ጋር እስከ 6 ወር ድረስ ውሉን ቢያድስም ባያድስም ስራውን የማሰራት መብቱ የተጠበቀ ነው።

12. በጨረታ ሰነድ ላይ ግልፅ ያልሆኑ ጉዳዮች ካሉ የማብራሪያ ጥያቄ በፅሁፍ ከጨረታው መክፈቻ 2 ወይም 3 ቀን በፊት ማቅረብ ይቻላል፡፡ በጨረታ ሰነድ መመሪያ ላይ በተጫራቹ የሚሞላ ሁሉንም ሰነድ መሞላት አለበት ሳይሞላ ቢቀር ጨረታው ላይ ውድቅ ቢሆኑ መስሪያ ቤቱ ሀላፊነት አይወስድም።

13. ተጫራቾች በጨረታው ሂደት ቅሬታ ካላቸው በት/ቤቱ ገንዘብ የግዥ እና አ/ጠ/አ/ሂሳብ/ደጋፊ የስራ ሂደት ቅሬታቸውን በጽሁፍ ማቅረብ ይችላሉ፡፡ በደጋፊ የስራ ሂደቱ የማይፈታ ከሆነ ደረጃውን ጠብቀው ለሚመለከተው አካል ማቅረብ ይችላሉ፡፡ የጨረታው ውጤት በተገለፀ በ7ቀን (ሰባት) ቀናት ውስጥ ቅሬታውን ያላቀረበ ተጫራች በውጤቱ እንደተስማማ ተቆጥሮ ስራው ከአሸናፊው ድርጅት ጋር ውል ይፈጽማል፡፡

14. አሸናፊው ድርጅት የስራውን ውል ከፈረመበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /ቀናት/ ውስጥ ስራውን መጀመር አለበት፡፡

15. የጨረታውን አካሄድ ለማዛባት የሚሞክር ማንኛውም ተጫራቾች ከጨረታው ውጪ ይሆናል፡፡

16. ማንኛውም ተጫራች ለሚያስገባቸው ዋጋ ቫትን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡

17. ተጫራቾች በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ ካደራጃቸው ወረዳ ህጋዊ ደብዳቤ በዕውቀቴ ወገኔ የመ/ደ/ት/በት ስም አፅፈው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

18. መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

19. ተጫራቾች በሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሰነድ ላይ የሚያቀርቡት የስራ አይነት ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ የሌለበት ስልጣን ባለው አካል የተፈረመባቸው የተሟላ አድራሻቸውን የሚገልጽ በህጋዊ ማህተም ያረፈበት ሊሆን ይገባል፡፡

 

አድራሻ፡- አዲስ ከተማ / ክ/ ከ/ ወረዳ 12 የዕውቀቴ ወገኔ ቅድመ መደበኛ ፣ አንደኛ ደረጃ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ከአጠና ተራ ወደ አስራ ስምንት በሚወስደው መንገድ 18 ሳይሻገር ድልድዩ ስር ይገኛል ፡፡

ለበለጠ መረጃ የስልክ ቁጥር፡- 011-2-73-90-66 ወይም 011-2-79-11-29

 

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 የዕውቀቴ ወገኔ ቅድመ መደበኛ ፣ አንደኛ ደረጃ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት

Save Tender