Tender Detail

Tender Details

  • Deadline24 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-01-24 00:00:00
  • Categories Spare Parts , Vehicle , Office Equipment

በፈዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ሥር በሚገኙ የተለያዩ የስራ ከፍሎች አገልግሎት ሠጥተው ተመላሽ የተደረጉ የቢሮ ዕቃዎች የግንባታ ዕታዎች፣ የተለያዩ መለዋወጫዎች አግልግሎት የሰጡ ተሽከርካሪዎች እና የተለያዩ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር አ/ዕ/ሽ 01/2018

በፈዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ሥር በሚገኙ የተለያዩ የስራ ከፍሎች አገልግሎት ሠጥተው ተመላሽ የተደረጉ የቢሮ ዕቃዎች የግንባታ ዕታዎች፣ የተለያዩ መለዋወጫዎች አግልግሎት የሰጡ ተሽከርካሪዎች እና የተለያዩ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ተጫራቾች

1. በፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ፋሲሊቲ ማናጅመንት ቢሮ ቁጥር 201 በመምጣት በኮርፖሬ፣ ሥር በሚገኙ የተለያዩ የስራ ከፍሎች አገልግሎት ሰጥተው ተመላሽ የተደረጉ የቢሮ፣ የግንባታ ፣ የተለያዩ እቃዎችን ዝርዝር የያዘውን መረጃ ተጫራቾች መመሪያ እና የዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የማ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00/ አንድ መቶ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፡፡

2. በዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ ላይ ተጫራቹ የሰጠው ዋጋ በሚለው ዓምድ ስር የሚገዙትን ንብረቶች ብቻ የጥቅል ዋጋ እንዲሰጥ እና የዋጋ 15% የተጨማሪ እሴት ታከስ በማሣየት በአሃዝ ያለስርዝ ድልዝ ገልጸው በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ ሥራ በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ፋሲሊቲ ማናጅመንት ቢሮ ቁጥር 201 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ማስገባት ይችላሉ፡፡ በየምድቡ ከተቀመጡት የጥቅል ዋጋ ዕቃዎች መካከል ተጫራቹ የሚፈልጋቸውን ዕቃዎች ብቻ መርጦ ዋጋ መስጠት አይችልም፤

3. ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመስርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡

4. ተጫራቾች ትከክለኛ አድራሻቸውንና ስማቸውን በታሸገው ኤንቨሎፕ እና በመጫረቻ ሠነዶቹ ላይ በማስፈር በፊርማ ማረጋገጥ ይጠበቅባቸዋል፤

5. ተጫራቾች ለሚገዙት ንብረት ያቀረቡትን ጥቅል የጨረታ ዋጋ ላይ 20 በመቶ (20%) በማስላት የጨረታ ማስከበሪያ ከባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት አያይዘው ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የሚዘጋጀው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒአ ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ ከሆነ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፎች ብቻ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

6. የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን ጠዋት በ4፡00 ሰዓት

ተዘግቶ በዛው ዕለት በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ተጫራቹ ከጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፡፡

7. ከጨረታው መዝጊያ ቀንና ሠዓት በኋላ የሚቀርቡ የመጫረቻ ሠነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡

8. የጨረታ መከፈቻ ቀን ቅዳሜ እና ዕሁድ ወይም በበዓል ቀን ላይ ከዋለ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡

9. የጨረታው ውጤት ለአሸናፊና ተሸናፊ ተጫራቾች በእኩል ጊዜ በጽሁፍ በኮርፖሬሽኑ የውስጥ ማስታወቂያ ሠሌዳና በደብዳቤ እንዲገለጽ ይደረጋል፡፡

10. ተጫራች የጨረታው ውጤቱ በኮርፖሬሽነ ዋና መ/ቤት የማስታወቂያ ሰሌዳ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ቅሬታ ካላቸው በ5 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በጽሁፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

11. በጨረታው ከፍተኛ ዋጋ በማቅረብ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች አሸናፊነታቸው በተገለፀላቸው በ 7 ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በመሉ መክፈል ይኖርባቸዋል፤ ሆኖም ሙሉ ከፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መከፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒአ ለኮርፖሬሽኑ ገቢ ይደረጋል፤

12. አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉበትን ገንዘብ አጠቃለው በመከፈል ዕቃዎቹን በ 10 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለባቸው፤ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በወቅቱ ካላነሱ የዕቃዎቹን ጠቅላላ ዋጋ 0.001% /1 /1000 በየቀኑ እየተሠላ በመቀጫነት እንዲከፍሉ ይደረጋል፤ ሆኖም የመቀጫው መጠን የጠቅላላውን ዋጋውን 10% ሲደርስ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለኮርፖሬሽነ ገቢ ተደርጎ አሸናፊነታቸው ይሠረዛል።

13. ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልከ ቁጥሮች 011-8-553627 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

14. ተጫራቾች ለጨረታው የሚሰጡት ዋጋ ከማንኛውም ግብር (Taxes) በፊት መሆን አለበት፡፡

15. ኮርፖሬሽኑ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን

Save Tender