Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Insurance Corporation (የኢትዮጵያ መድን ድርጅት)
  • Address Lagar, Ras Mekonen Ave, Addis Ababa, Ethiopia, Phone: 011-551 24 00
  • Websitehttps://eic-et.com/branches/
  • Deadline04 Feb 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-02-04 00:00:00
  • Categories Metals And Metal Working , Vehicle Spare Parts

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት አደጋ ደርሶባቸው ለደንበኞች ሙሉ የመድን ካሳ ከፍሎ ያስቀራቸውን በደሴ ዲስትሪክት ጋቢናዎችን በተናጠል፤ በጅምላ እና የተለያዩ የተሽከርካሪ ውጫዊና የውስጥ አካላት የተለያዩ ብረታ ብረቶችን ለመሸጥ ይፈልጋል።

Ethiopian Insurance Corporation (የኢትዮጵያ መድን ድርጅት)


የጨረታ ማስታወቂያ

 

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት አደጋ ደርሶባቸው ለደንበኞች ሙሉ የመድን ካሳ ከፍሎ ያስቀራቸውን በደሴ ዲስትሪክት ጋቢናዎችን በተናጠል፤ በጅምላ እና የተለያዩ የተሽከርካሪ ውጫዊና የውስጥ አካላት የተለያዩ ብረታ ብረቶችን ለመሸጥ ይፈልጋል።

በደሴ ዲስትሪክት የሚሸጡ ቁሳቁሶችና ጋቢናዎች በኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ከመናኸሪያው ፊት ለፊት በሚገኘው የዲስትሪክቱ ሪከቨሪ ግቢ በመገኘት ከጥር 13 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥር 27 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በመመልከት የጨረታ ማስከበሪያ ከኢትዮጵያ መድን ድርጅት ደሴ ዲስትሪክት (ETHIOPIAN INSURANCE CORPORATION DESSIE DISTRICT) ስም በተሠራ ሲ.ፒ.ኦ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።

የማስያዣ ዋጋው የጨረታ መነሻው 20 በመቶ ሲሆን ዝቅተኛ የማስያዣ ዋጋ ብር 1000 (ብር አንድ ሺህ) ነው።

•        ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታክስ በፊት በመሙላት የጨረታውን ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

•        ጥር 27 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በደሴ ዲስትሪክት ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው ጨረታው ጥር 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት በዲስትሪክቱ ቢሮ ይከፈታል።

በጨረታው ተሸናፊ ለሚሆኑ ተወዳዳሪዎች ጨረታ ማስከበሪያ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ከሁለት የስራ ቀናት በኋላ ተመላሽ የሚደረግ ሲሆን ለአሸናፊዎች ግን ሂሳቡ በገዙት ንብረት ላይ የሚታሰብ ሆኖ የገዙትን ንብረት ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ የገዙትን ዋጋ አጠናቀው በ 10 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን ባይረከቡ ለጨረታ ተሳትፎ ያስያዙት ገንዘብ በመቀጫ መልክ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ጨረታ ይሰረዛል።

ክፍያ ከፍለው ንብረቶቹን በተገለጸው ጊዜ የማያነሱ ተጫራቾች የጥበቃ ወጪ በቀን ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ይከፍላሉ። የጨረታው አሸናፊ በተቀመጠው ቀነ ገደብ ውስጥ ከከፈለ በኋላ ንብረቱን በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ ካላነሳ ከክፍያው ላይ የቅጣት ተቀንሶ ቀሪ ሂሳብ ካለው ተመላሽ ይደረግለታል።

ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ያሸነፈውን ጋቢና እና ቁሳቁስ በአለበት ሁኔታ በአንድ ጊዜ ማንሳት አለበት። ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ ማብራሪያ፡- ደሴ ዲስትሪክት 0333113020/0333123686/83

ደሴ ዲስትሪክት 0946000993/0911728111 መጠየቅ ይቻላል።

 

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት

Save Tender