Tender Detail

Tender Details

  • Company የተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት የቀድሞ ተማሪዎች ማኅበር (TMSAA)
  • Address የተፈሪ መኰንን ትምህርት ቤት የቀድሞ ተማሪዎች ማኅበር (TMSAA) ጽ/ቤት ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: +251 91 0007969
  • Website
  • Deadline10 Feb 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-02-10 00:00:00
  • Categories Construction Works

የተፈሪ መኰንን ትምህርት ቤት የቀድሞ ተማሪዎች ማኅበር (TMSAA) የትምህርት ቤቱን 100ኛ ዓመት (Centennial) ከብረ በዓል ምክንያት በማድረግ በትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገነባና ለትምህርት ቤቱ በስጦታ የሚበረከት ባለ 3 ፎቅ ሁለገብ ሕንፃ (Multi-purpose Building) በተለመደው የአርማታ ውቅር (Reinforced Concrete Framed (RC) ወይም በአማራጭ በብረት ውቅ

የተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት የቀድሞ ተማሪዎች ማኅበር (TMSAA)


የግንባታ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የተፈሪ መኰንን ትምህርት ቤት የቀድሞ ተማሪዎች ማኅበር (TMSAA) በኢትዮጵያ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቾች ባለሥልጣን (ACSO) ተመዝግቦ የሚንቀሳቀስ ሕጋዊ ሰውነት ያለው አካል ነው፡፡

ማኅበሩ የትምህርት ቤቱን 100ኛ ዓመት (Centennial) ከብረ በዓል ምክንያት በማድረግ በትምህርት ቤቱ ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገነባና ለትምህርት ቤቱ በስጦታ የሚበረከት ባለ 3 ፎቅ ሁለገብ ሕንፃ (Multi-purpose Building) በተለመደው የአርማታ ውቅር (Reinforced Concrete Framed (RC) ወይም በአማራጭ በብረት ውቅር (Cold Formed Steel (CES) ግንባታ ለማከናወን ይፈልጋል።

በመሆኑም ደረጃቸው BC-3 ወይም GC-3 እና ከዚያ በላይ የሆኑ፣ በኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ባለሥልጣን የተመዘገቡ የአገር ውስጥ የሥራ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል።

ጨረታው የኢትዮጵያን የፌዴራል የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ መመሪያዎችንና ሕጋዊ አሠራሮችን መሠረት አድርጎ የተዘጋጀ ነው፡፡

ተጫራቾች ከተጠቀሱት ዘዴዎች (Beinforced Concrete Framed (RC) ወይም (Cold Fomed Steel (CES) አንዱን መርጠው መወዳደሪያ ሠነዳቸውን ማቅረብ ይችላሉ።

ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መሠረታዊ መስፈርቶች፡-

•        በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ (Tax Clearance) እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው፡፡

•        የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡

•        በመንግሥት የግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ (PPA) የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ።

የጨረታው ዝርዝር ሁኔታ፡-

•        ተጫራቾች የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር) በማኅበሩ የባንክ ሒሳብ ቁጥር ገቢ በማድረግ ማሰረጃ ሲያቀርቡ፤ የጨረታ ሰነዱን የኤሌክትሮኒክ ቅጂ (Electronic Copy) ተፈሪ መኰንን ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ቅጥር ግቢ ውስጥ ከሚገኘው የማኅበሩ ጽሕፈት ቤት መውሰድ ይችላሉ።

•        ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) ብር 500,000 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም በሁኔታ ላይ ባልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Unconditional Bank Guarantee) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

•        ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ21 ቀናት ክፍት ሆኖ የሚቆይ ሲሆን፣ ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሠነዶቻቸውን በሰም በታሸገ ፖስታ እስከ የካቲት 3 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 6:00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ሣጥኑ ከቀኑ በ6:00 ሰዓት ታሽጎ በዚያኑ ቀን ማለትም የካቲት 3 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ በ8:00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

•        ማኅበሩ፤ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ጨረታውን በተመለከተ የጥያቄ መላኪያ አድራሻ

የተፈሪ መኰንን ትምህርት ቤት የቀድሞ ተማሪዎች ማኅበር (TMSAA) ጽ/ቤት

ስልክ:- +251 91 0007969/+251 910 012259

ኢሜይል:- tmsaacentennialbuilding@gmail.com

 

የተፈሪ መኮንን ትምህርት ቤት የቀድሞ ተማሪዎች ማኅበር (TMSAA)

 

Save Tender