የድሬዳዋ አስተዳደር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ባለስልጣን በድሬዳዋ አስተዳደር ውስጥ የG+2 ዋና መሥሪያ ቤት ህንፃ እድሳትና ሪኖቬሽን የኢርጎኖሚክስ እና የጉድጓድ ውሀ ቁፋሮ ሥራ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ትራንስፖርና ሎጅስቲክስ ባለስልጣን
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር ድ/ዳ/አስ/ት/ሎ/ባ 0007/2018
የድሬዳዋ አስተዳደር ትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ባለስልጣን በድሬዳዋ አስተዳደር ውስጥ የG+2 ዋና መሥሪያ ቤት ህንፃ እድሳትና ሪኖቬሽን የኢርጎኖሚክስ እና የጉድጓድ ውሀ ቁፋሮ ሥራ ተቋራጮችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ እና ብቃት ማረጋገጫ የ2018 ዓ.ም ያላቸውና የዘመኑን ግብርየከፈሉ (BC-1 Or GC2) ደረጃ እና ከተጠቀሰው በላይ
2. በመንግስት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ድህረ ገጽ ላይ በአቅራቢዎች ሊስት ውስጥ የተመዘገቡ፡፡
3. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና በጨረታ ለመሳተፍ የድጋፍ ደብዳቤ ያላቸው፡፡
4. የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከባለስልጣን መ/ቤቱ ዋና ገንዘብ ያዥና ከፋይ ቢሮ ቁጥር 19 መግዛት ይችላሉ፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ጥቅል 500,000.00 ብር (አምስት መቶ ሺ ብር) እውቅና ካለው ባንክ ሲ.ፒ.ኦ በድሬደዋ አስተዳደር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ባለስልጣን ስም አሰርተው ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
6. የጨረታው ሰነድ የተዘጋጀው በእንግሊዝኛ ቋንቋ ነው።
7. ማንኛውም ተጫራች በሌሎች ዋጋ ላይ በመመስረት የሚያቀርበው ዋጋ ተቀባይነት የለውም፡፡
8. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን በጨረታው ሰነዱ ውስጥ ይገለጻል፡፡
9. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋና የቴክኒክ ግምገማ ሰነድ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
10. ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ
ድሬ ዳዋ ቀበሌ 02 ጎሮ ዴልት ሆስፒታል ፊት ለፊት
ስልክ ቁጥር - 025 111 15 80 / 025 111 24 66
የድሬዳዋ አስተዳደር ትራንስፖርና ሎጅስቲክስ ባለስልጣን
