Tender Detail

Tender Details

  • Company ኢትዮ ተስፋ ከሕንጻ 011-022 የጋራ መኖሪያ ቤት ባለቤቶች ኃላ/የተ/ማኅበር
  • Address Addis Ababa, Phone: +251 911 75 28 24
  • Website
  • Deadline28 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-01-29 00:00:00
  • Categories Construction Works

ማኅበራችን ኢትዮ ተስፋ ከብሎክ 11 እስከ 22 የኮንዶሚኒየም የጋራ መኖሪያ ቤት ባለቤቶች ኃላፊነቱ የተወሰነ ማኅበር በኮዬ ፈጬ ፓርሴል 02 ከብሎክ 11 እስከ 22 ላሉት ብሎኮች የግቢ አጥር ግንባታ ማስገንባት ስለሚፈልግ በግንባታ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ የሥራ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የአጥር ግንባታ ማሰራት ይፈልጋል።

ኢትዮ ተስፋ ከሕንጻ 011-022 የጋራ መኖሪያ ቤት ባለቤቶች ኃላ/የተ/ማኅበር


ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ማኅበራችን ኢትዮ ተስፋ ከብሎክ 11 እስከ 22 የኮንዶሚኒየም የጋራ መኖሪያ ቤት ባለቤቶች ኃላፊነቱ የተወሰነ ማኅበር በኮዬ ፈጬ ፓርሴል 02 ከብሎክ 11 እስከ 22 ላሉት ብሎኮች የግቢ አጥር ግንባታ ማስገንባት ስለሚፈልግ በግንባታ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ የሥራ ተቋራጮችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የአጥር ግንባታ ማሰራት ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፦

1. በዘርፉ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

2. የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ፡፡

3. የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4. ተጫራቾች ለጨረታ የወጣውን ግንባታ ለማከናወን የሚያስችል፡-

4.1 በምን ያክል ጊዜ ግንባታውን ማጠናቀቅ እንደሚችሉ የሚያሳይ የሥራ መርሀ ግብር፣

4.2 የድርጅታችሁን በቂ የሰው ኃይል የሚያሳይ አደረጃጀት፤

4.3 በግንባታ ወቅት ከፍያ ቢዘገይ ግንባታው ሳይቆራረጥ እንዲቀጥል መተማመኛ የሚሆን የካፒታል አቅም መኖሩን ማረጋገጫ ወይም የቢዝነስ ፕላን ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ኮዬ ፈጬ 2 ፓርሴል 2 ብሎክ 13 ፓርኪንግ በሚገኘው የማኅበሩ ቢሮ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመከፈል ሰነዱን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10/ አስር / ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በከኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው የሚከፈት ይሆናል፡፡

ማሳሰቢያ፡-

1. ማኅበሩ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

2, የጨረታ ሰነድ ላይ ስርዝ ድልዝ ወይም የማይነበብ ካለ ተቀባይነት የለውም፡፡

3. ተጫራቾች የገዙትን ጨረታ ሰነድ በተዘጋጀለት የመስሪያ ነጠላ ዋጋ በማስገባት፣ የድርጅቱን ማህተም እና በድርጅቱ ኃላፊ ፊርማ በማሳረፍ በግልፅ አንድ ኦርጅናል እና አንድ ቅጂ በማለት በሁለት በታሸገ ፖስታ ከጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር:- +251 911 75 28 24 / +251 911 98 65 85 መደወል ይቻላል፡፡

ኢትዮ ተስፋ ከሕንጻ 011-022 የጋራ

መኖሪያ ቤት ባለቤቶች ኃላ/የተ/ማኅበር

Save Tender