Tender Detail

Tender Details

  • Deadline04 Feb 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price100.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-02-05 00:00:00
  • Categories Spare Parts

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት አደጋ ደርሶባቸው ለደንበኞች ሙሉ የመድን ካሳ ከፍሎ ያስቀራቸውን በደሴ ዲስትሪከት ጋቢናዎችን በተናጥል፤ በጅምላ እና የተለያዩ የተሽከርካሪ ውጫዊና የውስጥ አካላት የተለያዩ ብረታ ብረቶችን ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት አደጋ ደርሶባቸው ለደንበኞች ሙሉ የመድን ካሳ ከፍሎ ያስቀራቸውን በደሴ ዲስትሪከት ጋቢናዎችን በተናጥል፤ በጅምላ እና የተለያዩ የተሽከርካሪ ውጫዊና የውስጥ አካላት የተለያዩ ብረታ ብረቶችን ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

በደሴ ዲስትሪከት የሚሸጡ ቁሳቁሶችና ጋቢናዎች በኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ከመናኸሪያው ፊት ለፊት በሚገኘው የዲስትሪከቱ ሪከቨሪ ግቢ በመገኘት ከጥር 13 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥር 27 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በመመልከት የጨረታ ማስከበሪያ ከኢትዮጵያ መድን ድርጅት ደሴ ዲስትሪከት (ETHIOPIAN INSURANCE CORPORATION DESSIE DISTRICT) ስም በተሰራ ሲ.ፒ.ኦ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ፡፡

የማስያዣ ዋጋው የጨረታ መነሻው 20 በመቶ ሲሆን ዝቅተኛ የማስያዣ ዋጋ ብር 1000 (ብርአንድ ሺህ) ነው

➢ተጫራቾች የሚገዙበትን ዋጋ ከተጨማሪ እሴት ታከስ በፊት በመሙላት የጨረታውን ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

➢ ጥር 27 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በደሴ ዲስትሪከት ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው ጨረታው ጥር 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት በዲስትሪከቱ ቢሮ ይከፈታል፡፡

በጨረታው ተሸናፊ ለሚሆኑ ተወዳዳሪዎች ጨረታ ማስከበሪያ ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ከሁለት የስራ ቀናት በኋላ ተመላሽ የሚደረግ ሲሆን ለአሸናፊዎች ግን ሂሳቡ በገዙት ንብረት ላይ የሚታሰብ ሆኖ የገዙትን ንብረት ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ የገዙትን ዋጋ አጠናቀው በ 10 ቀናት ጊዜ ውስጥ ንብረቱን ባይረከቡ ለጨረታ ተሳትፎ ያስያዙት ገንዘብ በመቀጫ መልከ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ጨረታ ይሰረዛል፡፡

ከፍያ ከፍለው ንብረቶቹን በተገለጸው ጊዜ የማያነሱ ተጫራቾች የጥበቃ ወጪ በቀን ብር 100 (አንድ መቶ ብር) ይከፍላሉ፡፡ የጨረታው አሸናፊ በተቀመጠው ቀነ ገደብ ውስጥ ከከፈለ በኋላ ንብረቱን በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ ካላነሳ ከከፍያው ላይ የቅጣት ተቀንሶ ቀሪ ሂሳብ ካለው ተመላሽ ይደረግለታል፡፡

ማንኛውም ተጫራች በጨረታ ያሸነፈውን ጋቢና እና ቁሳቁስ በአለበት ሁኔታ በአንድ ጊዜ ማንሳት አለበት፡፡ ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ ማብራሪያ፦ ደሴ ዲስትሪክት 0333113020/0333123686 / 83

ደሴ ዲስትሪክት 0946000993/0911728111 መጠየቅ ይቻላል፡፡

የኢትዮጵያ መድን ድርጅት

Save Tender