Tender Detail

Tender Details


በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በኮንሶ ዞን የኮልሜ ወረዳ ፋይናንስ ጽህፈት ቤት በ2018 ዓ.ም. በጀት ዓመት የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድረው ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል

በስልጤ ዞን የስልጢ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት


የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ የግዥ ቁጥር (002 ግ/ዥ 01/05/ 2018)

 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በኮንሶ ዞን የኮልሜ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 ዓ/ም በጀት ዓመት በመንግሥት መደበኛ እና ካፒታል ገንዘብ ምንጭ ከወረዳ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የተሰበሰበው የ2018 ዓመታዊ የግዥ ፍላጎት ዕቅድ መሠረት የኤሌክትሮኒክስ፤ የጽ/መሣሪያ አላቂ ሌሎች አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የፈርኒቸር፤ የፋብሪካ ውጤቶች እና የሞተር ሣይከል ዓይነቶች ግዥ በዘርፋ የተመዘገቡ ህጋዊ አቅራቢያዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድረው ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል።

 በዚህ መሠረት በጨረታው ላይ ለመወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች በሙሉ፡-

1.       በዘርፉ የዘመኑን ግብር የከፈሉ/የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፤

2.       በዘርፉ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው

3.       በዘርፉ/ TIN Number/ የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት ያላቸው

4.       የተጨማሪ እሴት ታክስ/ Vat/ ተመዘጋቢ የሆኑ፤

5.       በዘርፉ የአቅራቢነት የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው

6.       በማህበር የተደራጁ ከሆነ ህጋዊ የሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ያላቸው

7.       የኤሌክትሮኒከስ፤ የጽ/መሣሪያ አላቂና ሌሎች አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፣ የፈርኒቸር የፋብሪካ ውጤቶች እና የሞተር ሣይክል ዓይነቶች የግዥ የተዘጋጀው የተለያዩ ዝርዝር የጨረታ ሠነዶች /Specification/ የያዘ የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ለእንዳንዱ ጨረታ ሠነድ ሁለት መቶ ብር /200/ በመክፈል ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ በኮልሜ ወረዳ ገቢዎች ጽ/ቤት የሠነድ ሽያጭ ገንዘብ በመክፈል በወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዥና ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 01 መቅረብ ሠነዱን መውሰድ ይችላል።

8.       ዕጩ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ ዋስትና ከታወቀ ባንከ የሚሰጥ የክፍያ ማዘዣ ወይም በጥሬ ገንዘብ ይሆናል። ስለዚህ ለኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ 30,000/ ሰላሣ ሺህ ብር/፤ የጽ/መሣሪያ አላቂና ሌሎች አላቂ የቢሮ ዕቃዎች 25,000/ሃያ አምሰት ሺህ ብር/ ፤ ለፈርኒቸር ግዥ 20,000/ሃያ ሺህ ብር/፣ ለፋብሪካ ውጤቶች ግዥ 25,000/ሃያ አምስት ሺህ ብር/እና ለተለያዩ የሞተር ሣይክል ዓይነቶች ግዥ 25,000/ሃያ አምስት ሺህ ብር/ የቴክኒካል ኦርጅናል መረጃዎች ጋር በፖስታ አሽገው ለኮልሜ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ብሎ በአድራሻ በመፃፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

9.       ተጫራቾች የጨረታ ሠነድ በአንድ ኤንቨሎፕ የሚቀርብ ሆኖ ቴክኒካልና ፋይናንሻል እያንዳንዳቸው አንድ አንድ ኦርጅናልና 1 ኮፒ በማድረግ የጨረታ ማስከበሪያ በተክኒካል ኦርጅናል ፖስታ ጋር በትክክል በታሸገው በአንድ ኤንቨሎፕ የእናት ፖስታ ውስጥ በማስገባት በማሸግ ማህተም በማሳረፈ፤ አድራሻ በመግለጽና በመፈረም ጨረታው የሚታሸገው 16ኛው የሥራ ቀን ልክ 6፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 10፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች አከፋፈትን በተመለከተ የቴክኒካል ኤንቨሎፕ ፖስታ መጀመሪያ ደረጃ ግምገማ ይካሄዳል፡፡ ቀጥሎ የፋይናንሻል ኤንቨሎፕ ፖስታ በመመሪያ መሠረት ተከፍቶ ግምገማው በመመሪያ ለግዥው የተዘጋጀው በመደበኛው የጨረታ ሠነድ መሠረት የሚካሄድ ይሆናል።

10.   ሌሎች ተጫራቾች በሚያቀርቡ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ የተከለከለ ነው።

11.   አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን የውል ማስከበሪያ ሠነድ 10% በማስያዝ ባሸነፉበት የጨረታ መሠረት የሥራ የውል ማስከበሪያ ወይም ቅድመ ክፍያ የሚከፍል ከሆነ ተመጣጣኝ የቅድመ ክፍያ ዋስትና ይዘው ቀርበው 15 የሥራ ቀናት ውስጥ ውል ባይገባ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግሥት ውርስ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል።

12.   ተጫራቾች ጨረታው ይከፈታል በተባለው በ16ኛው ቀን በመንግስት የሥራ ቀን ላይ ካልዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሣሣይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

13.   ተጫራቾች ተሟልተው ያለመገኘት የጨረታው አከፋፋት ሥነ-ሥርዓት ሊያስተጓጉል አይችልም።

14.   ተጫራቾች የመንግስት ግዥ መመሪያ በሚያዘው መሠረት ጨረታው የሚከፈትበት ዕለት ጀምሮ የጨረታ ዋጋ ፀንቶ የሚቆይበት ለ30/ሰላሳ/ ቀናት ይሆናል።

15.   መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በመሉ የመረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ ፡-09 12 13 66 45/ 09 53 76 45 67/ ደውለው ይጠይቁ

በኮንሶ ዞን የኮልሜ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት /ደልቤና/

Save Tender