Tender Detail

Tender Details

  • Company Debre Birhan Wood Processing Pvt. Ltd (የደ/ብርሀን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር)
  • Address ደብረ ብርሃን ከተማ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011637 58 03
  • Website
  • Deadline26 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-01-26 00:00:00
  • Categories Wood And Wood Working , Raw Materials , Industry And Factory

የደብረብርሀን እንጨት ማቀባበሪያ ኃ/የተ/ የግል ለዚህ ምርት ግብዓት የሚሆን 120 ቶን ግሉ ፓውደር /Urea formaldehyde powder resin glue/ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

Debre Birhan Wood Processing Pvt. Ltd (የደ/ብርሀን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር)


በድጋሚ የወጣ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

 

የደብረብርሀን እንጨት ማቀባበሪያ ኃ/የተ/ የግል ለግንባታ መስሪያ እና ለፈርኒቸር የሚሆን ጥራት ያለው ፕለይ ውድ ጣውላ አምራች ድርጅት ነው። ስለሆነም ፋብሪካው ለዚህ ምርት ግብዓት የሚሆን 120 ቶን ግሉ ፓውደር /Urea formaldehyde powder resin glue/ በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት

1.     በትክክለኛው የስራ መስክ የተሰማራና የንግድ ስራ ፈቃዱን ያሳደሱ እና ስድስት ወር ያላለፈው ጨረታ ለመሳተፍ የሚያበቃ የነቢዎች የጨረታ ከሊራንስ ማቅረብ የሚችሉ

2.     የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነምበር/ ያላቸው

3.     የቫት ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፣

4.     ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትና ሌሎች የሚመለከታቸው ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፣

5.     የጨረታው ዝርዝር መረጃ በጨረታ ሰነዱ ላይ ይገኛል፣

6.     ተጫራቾች ለግሉ ፓውደር ጨረታ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ 400,000.00 (አራት መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ /CPO/ ማስያዝ አለባቸው፤

7.     ተጫራቾች በሚያቀርቡት ሰነድ ላይ ስማቸውን ፊርማቸውንና አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው።

8.     በመጫረቻ ሰነድ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም ካለም አንድ ስርዝ በማድረግ ፊርማቸውን ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡

9.     ማንኛውም ተጫራች ኦርጅናል የጨረታ ሰነድ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ለተከታታይ 16 ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታውን ሰነድ ገቢ ማድረግ ይችላሉ፡፡

10. ጨረታው ተጫራቾች ወይ ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን /ጨረታው በተዘጋበት ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ላይ በካምፓኒው የፋይናንስ ቢሮ ውስጥ በይፋ ይከፈታል። ተጫራቾች ባይገኙም ከመከፈት አይታግድም፡፡

11. የመክፈቻ ቀኑ እሁድ ወይም በህዝብ በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል፤

12. አሸናፊ ሆኖ የተመረጠው ተጫራች የውል ማስከበሪያ የሚሆን ገንዘብ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና የአሸነፈበትን ጠቅላላ 10% ማስያዝ አለበት።

13. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከካምፖኒው የፋይናንስ ቢሮ መውሰድ ይችላሉ፡፡

14. ከተጠቀሰው ብዛት ወይም መጠን በታች ቀንሶ መጫረት አይቻልም፡፡

15. አቅራቢ ድርጅቱ የማስጫኛ እና የማስወረጃ እንዲሁም ሌሎች ወጪዎችን ሸፍኖ ንብረቱን ለካምፓኒው ንብረት ክፍል ያስረክባል፡፡

16. ካምፓኒው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በመሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-637-5803 ደውለው ይጠይቁ

 

የደ/ብርሀን እንጨት ማቀነባበሪያ ኃ/የተ/የግል ማህበር

ደ/ብርሀን

 

Save Tender