Tender Detail

Tender Details

  • Company የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አፋር ሪጀን
  • Address አፋር ፣ኢትዮጲያ, Phone: 0333668336
  • Website
  • Deadline05 Feb 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price1000.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-02-05 00:00:00
  • Categories Vehicle

የአፋር ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት ንብረት የሆነ የተለያዩ ያገለገሉ 07 ተሸከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አፋር ሪጀን


የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር EEU-AFR-S-C &

PGS-002/2018

የፋር ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት ንብረት የሆነ የተለያዩ ያገለገሉ 07 ተሸከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ እና ቦታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም በጨረታ መካፈል የሚፈልግ ድርጅት ወይም ግለሰብ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡

1. ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን | ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በድርጅታችን አካውንት ቁጥር (EEU AFAR REGION Account No.1000150711235) የማይመለስ ብር 1,000.00(አንድ ሺህ ብር) ገቢ በማድረግ በአፋርሪጅን ሳፕላይ ቼን ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ በመምጣት የተሽከርካሪዎችን ዝርዝር መረጃ የያዘ የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡

2. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ገዝተው ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት፣ ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 9፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ተሸከርካሪዎችን ሰመራ በሚገኘው የድርጅቱ ጋራዥ በመሄድ መመልከት ይችላሉ፡፡

3. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት ተሸከርካሪ ለእያንዳንዱ የጨረታ መነሻ ዋጋ 20 በመቶ (20%) የተለያየ የጨረታ ማስከበሪያ በባንከ በተረጋገጠ ሲፒኦ(CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና (Bid Bond) በአፋር ሪጅን ኤሌክትሪከ አገልግሎት (AFAR REGION ELECTRIC UTILITY) ስም ከመወዳደሪያ ሰነዳቸው ጋር በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ የጨረታ ቁጥሩን በመግለፅ ጥር 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ አፋር ሪጅን ሳፐላይ ቼን ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

4. ጨረታው ጥር 28 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያው ቀን በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት አፋር ሪጅን ሳፕላይ ቼን ንብረትና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ይከፈታል፡፡

5. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ መሆን አለበት።

6. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልከ ቁጥር 033-33-66-83-36/09-47-74-75-76 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

7. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የአፋር ሪጅን ኤሌክትሪክ አገልግሎት

Save Tender