ድርጅታችን ፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ ቃሊቲ ብረታ ብረት ፋብሪካ በዋናው መ/ቤት ባለው ይዞታ ውስጥ አስተማማኝ፣ ቀጣይነት እና ከፍተኛ የጥራት ደረጃ ያለው የከርሰ ምድር ውሃ የሚገኝበትን ስፍራ ለይቶ የሚያጠና ድርጅት በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
Tsehay Industry S.C. Kaliti Metal Products Factory (ፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ ቃሊቲ ብረታ ብረት ፋብሪካ)
ፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ
TSEHAY INDUSTRY S.C.
ቃሊቲ ብረታ ብረት ፋብሪካ
KALITI METAL PRODUCTS FACTORY
Document No. OF/KMPF/254 (Pr No 008)
የጉድጓድ ውሃ ቁፋሮ ለማከናወን የሚያጠና ባለሙያ /ድርጅት ለመቅጠር የወጣ ግልፅ ጨረታ ቁጥር 10/2018
ድርጅታችን ፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ ቃሊቲ ብረታ ብረት ፋብሪካ በዋናው መ/ቤት ባለው ይዞታ ውስጥ አስተማማኝ፣ ቀጣይነት እና ከፍተኛ የጥራት ደረጃ ያለው የከርሰ ምድር ውሃ የሚገኝበትን ስፍራ ለይቶ የሚያጠና ድርጅት በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም፡-
1. ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፤ የፀና የሙያ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ መለያ ስርተፊኬት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
2. ተጫራቾች ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ቃሊቲ መናኸሪያ አካባቢ ከካፍደም ነዳጅ ማደያ ወደ ውስጥ 700 ሜትር ገባ ብሎ በሚገኘው ከድርጅቱ የግዢ ዋና ክፍል የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይቻላል፡፡
3. በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያለው ተጫራች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በመውሰድ በጨረታው የሚወዳደሩበት የቴክኒካል እና የፋይናንሺያል ሰነዶቻቸውን ለየብቻ በታሸገ ፖስታ በማድረግ እስከ ጥር 19 ቀን 2018 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት በፊት ዘወትር በስራ ሰዓት ከላይ በተገለፀው አድራሻ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲፒኦ ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ከጨረታ ሰነዳቸው የቴክኒካል ፖስታ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
5. ጨረታው ጥር 19 ቀን 2018ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 በድርጅቱ ዋና መ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
6. ድርጅቱ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለተጨማሪ መረጃ/ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 011 4 34 03 87 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
ፀሐይ ኢንዱስትሪ አ.ማ
