Tender Detail

Tender Details

  • Deadline31 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price400.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-01-31 00:00:00
  • Categories Construction Works

በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን በገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ለጎራ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።


ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ሀገር አቀፍ

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

መለያቁጥር GGWW/008/2018

በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን በገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ለጎራ ከተማ ማዘጋጃ ቤት ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

ስለሆነም ተጫራቾ

1. የዘመኑን ንግድ ፍቃድ ያሳደሱ የቫት እና ቲን ነምበር ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።

2. በጨረታው ለመወዳዳር የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች የሚገዙት ጨረታ ሰነዱን ጠቅሰው በማመልከቻ ይዘው መምጣት አለባቸው ።

3. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 20ኛው ተከታታይ ቀናት እስከ 8፡00 ሰአት ድረስ የማይመለስ ብር 400 /አራት መቶ/ ብር ብቻ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ መሀልአምባ ከተማ ገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ድረስ በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡

4. የመወዳደሪያ ደረጃቸውም GC/BC ደረጃ 5 እና ከዛ በላይ የሆኑ ተቋራጮች ።

5. የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ 100000/አንድ መቶ ሺህ/ ብቻ በገ/ጉ/ወ/ወ/ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም ማሰራት አለባቸው።

6. ተጫራቾች የጫረታውን ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመንት ሀ/ ለቴከኒካል ዶክመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ቴከኒካል በሚል በመለየት ለ/ ለፋይናንሻል ዶከመንት አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ፎቶ ኮፒ በማድረግ ፋይናንሻል በሚል በመለየት በሰም በማሸግ ከላይ በተጠቀሰው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ /ከባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ከቴከኒካል ኦርጅናል ዶክመንቱ ጋር በማድረግ በሰም በማሸግ ቴከኒካል ዶክመንት በሚል በመለየት ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 20(ሀያ) ተከታታይ ቀናት መሀል አምባ የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር -03 ድረስ በመምጣት ለጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።

7 የጨረታው ሰነድ በ20ኛው ተከታታይ ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ይታሸጋል ። ከቀኑ 8፡30 ተጫራቾች በተገኙበት ይከፈታል፡፡

8. መስሪያቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ ፡-1. በአፈፃፀም ምከንያት ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ድርጅቶች መወዳደር አይችሉም።

2. በወረዳው ውስጥ ፕሮጀከት ይዞ ስራውን ያልጨረሰ ተጫራች እና በውክልና ሰነድ ገዝቶ መወዳደር አይችልም። 3.ተጫራቾች ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ከአሰሪው መስሪያ ቤት የሳይት ምልከታ ማየታቸውን የሚገልጽ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉና መሆን አለባቸው።

4. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በአል ወይም ቅዳሜ ና እሁድ ከሆነ ወደ ሚቀጥለው የስራ ቀን ይዘዋወራል።

ለበለጠመረጃ፡- የገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ

ስልክ ቁጥር 0113360162/146 ይደውሉ

መሀል አምባ

ጉራጌ ዞን በገ/ጉ/ወ/ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

Save Tender