ዘርፋቸን ለ2018 በጀት ዓመት በዘርፉ ሥር ለሚገኙ ለአዳማ፣ አሰላ፣ ደ/ማርቆስ እና ጅማ ጥበይት ማዕከል የሠራተኞች የደንብ ልብስ እና የአደጋ መከላከያ መሳሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡
የኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የእህልና ቡና ንግድ ሥራ ዘርፍ
ግልጽ የጨረታ ወስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- እ.ቡ.ን.ሥ.ዘ የደ/ ልብ/የአይ/መከ/ግጨ 01/2018
ዘርፋቸን ለ2018 በጀት ዓመት በዘርፉ ሥር ለሚገኙ ለአዳማ፣ አሰላ፣ ደ/ማርቆስ እና ጅማ ጥበይት ማዕከል የሠራተኞች የደንብ ልብስ እና የአደጋ መከላከያ መሳሪዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ ለመፈፀም ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው ላይ መወዳደር የሚፈልጉ ድርጅቶች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መመዘኛዎች ማሟላት አለባቸው::
❖ የሠራተኛ የደንብ ልብስ እና የአደጋ መከላከያ ግዥ
1. ተጫራቾች በዘርፋ ለ2018 በጀት ዓመት የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ ምስከር ወረቀት፣ የአቅራቢነት ምዝገባ የምስከር ወረቀት፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ወቅታዊ ከሊራንስ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት እና የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ እነዚህ ሰነዶች በቴክኒካል ፕሮፖዛል ፖስታ ውስጥ ታሽገው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
2. ተጫራቾች ከላይ የተገለጹትን ሰነዶች ከጨረታ ሰነድ ማቅረቢያው ቀነ ገደብ በፊት ማቅረብ አለባቸው፡፡
3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 350.00(ሶስት መቶ ሃምሳ ብር) በመከፈል ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጥር 11 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00 - 6፡00 ሰዓት እንዲሁም ከሰአት ከ7፡00 - 10፡30 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ከጠዋቱ 2፡00- 6፡00 ሰዓት ድረስ የዘርፉ ዋናው መ/ቤት ብሎከ 1 ቢሮ ቁጥር 12 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡ (አድራሻው ከስር ተገልጿል)
4. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን እስከጨረታው መዝጊያ ዕለት እስከ የካቲት 2 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
5. ተጫራቾች ከላይ ለተጠቀሰው ጨረታ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 50,000.00 ሃምሳ ሺህ ብር/ በሲፒአ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን እህልና ቡና ንግድ ዘርፍ ስም አሰርተው ለብቻው በፖስታ ተለይቶ ከፖስታው ላይ የጨረታ ማስከበሪያ በሚል ተገልፆ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ አለባቸው::
6. የጨረታ ማስከበሪያው በቴከኒካል ፕሮፖዛል ፖስታ ውስጥ ወይም ለብቻው ታሽጎ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
7. ተጫራቾች የቴከኒክ መወዳደሪያ ሰነዳቸውንና ዋጋ የሞሉበትን የጨረታ መወዳደሪያ ሀሳባቸውን በግልጽ ከፋፍለው በተለያየ ኤንቨሎፕ ለየብቻ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
8. ጨረታው የካቲት 2 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:00 ከሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኮርፖሬሽኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
9. ከዋና የመወዳደሪያ ሀሳብ (አርጅናል) በተጨማሪ የሚፈለጉ ኮፒዎች ብዛት (አንድ)
10. አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ 10% (አስር ፐርስንት) በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና በኢትዮጵያ ንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን እህልና ቡና ንግድ ሥራ ዘርፍ ስም አሰርተው ውሉን የሚፈጽሙ ይሆናል፡፡
11. ዘርፉ ጨረታውን በከፊልም ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ተጫራቾች ለማንኛውም ማብራሪያ በአካል በመቅረብ ወይም በስልክበመደወል መጠየቅ ይቻላሉ፡፡
አድራሻ፡- ደብረዘይት መንገድ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጠመንጃ ያዥ ቅርንጫፍ ፊት ለፊት
ስልክ ቁጥር 0114663951/ 011 4663958
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
በኢትዮጵያ የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን የእህልና ቡና ንግድ ሥራ ዘርፍ
