የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የተለያየ መጠን ያላቸው ያገለገሉ ትራንስፎርመሮች በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል (Ethiopian Electric Power)
የጨረታ ማራዘሚያ
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በጨረታ ቁጥር ኢኤአ/ንአ/ግጨ 05/2018 ታህሳስ 05 ቀን 2018 ዓ.ም በወጣው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ብዛታቸው 438 የሆነ የተለያዩ መጠን ያላቸው ያገለገሉ ትራንስፎርመሮችን ለመሸጥ ጨረታ ማውጣቱ ይታወሳል፡፡
ስለሆነም የጨረታ መዝጊያው እና መክፈቻው ከዚህ በታች በተጠቀሰው መሠረት የተራዘመ መሆኑን እንገልፃለን።
|
ሎት |
የሚወገደው ንብረት ዓይነት |
የሚገኝበት ቦታ |
ብዛት |
ቀደም ሲል የነበረው የጨረታ መዝጊያ |
ቀደም ሲል የነበረው የጨረታ መክፈቻ |
የተሻሻለው ጨረታ መዝጊያ |
የተሻሻለው ጨረታ መክፈቻ |
|
2 |
የተለያየ መጠን ያላቸው ያገለገሉ ትራንስፎርመሮች |
ኮተቤ ኤሌክትሪካል ወርክ ሾፕ |
631 |
ጥር 06 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 |
ጥር 06 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 |
ጥር 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 |
ጥር 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 |
ስለሆነም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ድርጅት ወይም ግለሰብ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
1. ተጫራቾች ዝርዘር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በድርጅታችን አካውንት ቁጥር (EELU Minor Account No, 1000068699332) የማይመለስ ብር 300 (ሦስት መቶ ብር) ገቢ በማድረግ ዘወትር በስራ ሰዓት ሜክሲኮ አዲስ አበባ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት በሚገኘው የንብ ባንክ ዋናው መ/ቤት 10ኛ ፎቅ ንብረት አስተዳደር ቢሮ በመምጣት የሚወገዱትን ንብረቶች ዝርዝር መረጃ የያዘ የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
2. ተጫራቾች ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነድ ገዝተው ዘወትር በስራ ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት፣ ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት እስከ 10፡00 ሰዓት ባለው ጊዜ ውስጥ ንብረቶቹ በሚገኙበት ቦታ በመሄድ መመልከት ይችላሉ፡፡
3. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ የሚያቀርቡት የገንዘብ መጠን በባንክ በተረጋገጠ (CPO) ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Security) ብር 300,000 (ሦስት መቶ ሺህ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን እና የጨረታ ማስከበሪያቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ስማቸውን እና ጨረታ ቁጥሩን በመግለፅ ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ድረስ ብቻ በተጠቀሰው አድራሻ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
5. ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻው በተገኙበት ሜክሲኮ አዲስ አበባ ንግድ ስራ ኮሌጅ ፊት ለፊት በሚገኘው የንብ ባንክ ዋና መ/ቤት 10ኛ ፎቅ ንብረት አስተዳደር በሚገኘው ቢሮ ይከፈታል፡፡
6. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ 15% ተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ መሆን አለበት፡፡
7. ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 011-1-26-52-55/011-1-70-01-18 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
8. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት
