ድርጅታችን ሴቭ ዘ ሩራል ሶሳይቲ የተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ግብረ ሠናይ ድርጅት እ.ኤ.አ በ ዲሴምበር 31/2025 የተገባደደው በጀት ዓመት ያከናወናቸው ሥራዎች እና የሂሳብ ሰነዶች በውጭ ኦዲተር በGAAP አማካኝነት አመታዊ ኦዲት ሪፖርት (Statutory Audit Report) ማሰራት ይፈልጋል፡፡
ሴቭ ዘ ሩራል ሶሳይቲ
ለኦዲት ስራ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ሴቭ ዘ ሩራል ሶሳይቲ የተባለ መንግስታዊ ያልሆነ ግብረ ሠናይ ድርጅት በኢፌዴሪ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አዋጅ ቁጥር 1113/2011 መሰረት በመዝገብ ቁጥር 0606 የተመዘገበ ሲሆን፤ የአርብቶ አደሩ እና ከፊል አርሶ አደሩ የማህበረሰብ ክፍሎች በመደገፍ ላይ የሚገኝ ድርጅት ሲሆን፤ በድርቅና በተፈጥሮ አደጋዎች ላቢያ የሚጎዱ ወገኖች ለመርዳትና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች በትጋት በመስራት በተለያዩ የሶማሌና ኦሮሚያ ክልል ዞኖች እና ወረዳዎች በመንቀሳቀስ ላይ እንገኛለን፤ በተለይም ባለፉት ሰባት (7) አመታት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ሲናበረክት ቆይተናል፡፡
በዚህ መሠረት ድርጅታችን እ.ኤ.አ በ ዲሴምበር 31/2025 የተገባደደው በጀት ዓመት ያከናወናቸው ሥራዎች እና የሂሳብ ሰነዶች በውጭ ኦዲተር በGAAP አማካኝነት አመታዊ ኦዲት ሪፖርት (Statutory Audit Report) ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ድርጅቱ እንዲመረመርለት ያቀረበው የቦከስ ፋይል ብዛት በቁጥር 03 (ሶስት) ሲሆን ለመወዳደር የሚፈልግ ኦዲተር/ ኦዲት ፊርም የሚከተሉትን ነጥቦች ማሟላት ይኖርበታል፡፡
1. የኦዲተርነት የሙያ ማረጋገጫ ያለው ያላት
2. የንግድ ፈቃድ ያለው ያላት
3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው/ ያላት
4. የዘመኑን ግብር ስለመክፈሉ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል/ የምትችል
5. ከፌዴራል ወይም ከክልል የኦዲት መሥሪያ ቤት ለበጀት ዓመቱ የታደሰ ፈቃድ እና ሌሎች አስፈላጊ ሰነዶች ማቅረብ የሚችል/ የምትችል ሲሆን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ሦስት (3) ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ አስፈላጊ የሆነ ሰነዶችንና የምትሰሩበትን ዋጋ የያዘ ሰነድ በማቅረብ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገለፃለን፡፡
አድራሻ፡- ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ መንገድ ወረድ ብሎ፤ ጅግጅጋ
ለበለጠ መረጃ፡- ስ.ቁ +251 915082980/ +251 915741249
ኢ-ሜይል:- savetheruralsociety@gmail.com
ሴቭ ዘ ሩራል ሶሳይቲ
