Tender Detail

Tender Details

  • Company በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ
  • Address የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወራቤ ቅርንጫፍ ሕንፃ 1ኛ ፎቅ : በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት : ኢትዮጵያ, Phone: 0467 71 11 80
  • Website
  • Deadline29 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-01-29 00:00:00
  • Categories Education And Training , Electrical/Electronics Educational And Training Equipment

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ለ2018 በጀት ዓመት ቢሮው የኤሌክትሮኒክስና አድቫንስ የኢኮቴ ባለሙያዎች ሥልጠና አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ


ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ለ2018 በጀት ዓመት ቢሮው የኤሌክትሮኒክስና አድቫንስ የኢኮቴ ባለሙያዎች ሥልጠና አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-

1.     የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣

2.     የዘመኑን ግብር የከፈሉና አግባብ ያለው የታደሰ የንግድ ፊቃድ ያላቸው፣

3.     በፋይናንስ መስሪያ ቤቶች በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ እና በሕግ ያልተገደቡ፣

4.     ለእያንዳንዱ ዕቃና አገልግሎት ግዥ በቢሮው የተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ ዘወትር በሥራ ሰዓት ከቢሮው የግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 10 በመቅረብ የማይመለስ ብር 300 በመክፈል መግዛት ይችላሉ።

5.     ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ የቴክኒካል የጨረታ ሰነድና የፋይናንሻል የጨረታ ሰነድን ለየብቻ ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን ለእያንዳንዱ ተመሳሳይ አንድ አንድ ኮፒዎች አዘጋጅተው በየኢንቨሎፑ የውጭ ገጽ ዋና (ኦርጅናል) ወይም ኮፒ ብሎ በመፃፍና አሽገው ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

6.     በማንኛውም ኢንቨሎፕ ውስጥ የጨረታ ማስከበሪያ ማስገባት ያለባቸው ምሳሌ ተጫራቾች የንግድ ፈቃድ፣ የቫት ሰነድ፣ መልካም የስራ አፈጻጸም ወዘተ መካተት ያለባቸው በቴክኒክ የጨረታ ሰነድ በሆኑት በዋናው ኦርጅናል እና ኮፒ ተብሎ በተገለጹት በሁለቱም ኢንቨሎፕ ሲሆን በፋይናንስ የጨረታ ሰነድ በዋናው ኦርጅናል ሆኖ ኮፒ ኢንቨሎፕ ውስጥ ከፋይናንስ የጨረታ ሰነድ ውጭ ምንም ተጨማሪ መረጃ ማስገባት አይፈቀድም።

7.     ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን የሚያስገቡበት የመጨረሻ ቀን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ለ15 የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ብቻ ሰነዱ የሚሸጥ ይሆናል። ጨረታው በ15ኛው ቀን ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮው በግልጽ ይከፈታል። ሆኖም 15ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ ጨረታው የሚዘገውና የሚከፈተው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ ይሆናል።

8.     ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ CPO የባንክ ጋራንት ሌተር ኦፍ ክሬዲት ዋስትና ማስያዝ ይኖርባቸዋል።

9.     ቢሮው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።

10. የኤሌክትሮኒክስና አድቫንስ የኢኮቴ ባለሙያዎች ሥልጠና አገልግሎት ዝርዝር መረጃ ከጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተያያዘና የተገለጸ በመሆኑ ዝርዝሩን ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል።

አድራሻ፡- የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ወራቤ ቅርንጫፍ ሕንፃ 1ኛ ፎቅ

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0467 71 11 80/ 0467 71 08 49 ይደውሉ።

 

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ

Save Tender