የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕላንና ልማት ቢሮ የ2018 በጀት አመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የሲዳማ ብ/ክ/መ/ፕላንና ልማት ቢሮ
ሁለተኛ ዙር የጨረታ ማስታወቂያ
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕላንና ልማት ቢሮ የ2018 በጀት አመት ለቢሮ አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች በሎት የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
ሎት 01 ኤሌክትሮኒክስ
ሎት 02 የሞተር ሳይክል።
በዚሁ መሠረት ተወዳዳሪዎች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች በሟሟላት መሣተፍ ይችላሉ።
1. ተጫራቾች በዚሁ የንግድ ስራ ዘርፍ የተሰማሩ ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉበትን ማስረጃ እንዲሁም የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
2. በገቢዎች ሚኒስተር የምዝገባ ሠርተፍኬት የታክስ ከፋይ መለያ ቁጥርና የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
3. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 15 ተከታታይ ቀን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 209 በመምጣት የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር ብቻ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
4. ማንኛውም ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር ሎት 01 ለኤለክትሮኒክስ/ 10,000/አስር ሺህ ብር/ ብቻ ሎት 02 /ለሞተር ሳይክል/ 10,000/አስር አምስት ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረለት /ሲፒኦ/ ብቻ ከጨረታ ተክንካል ኦርጅናልና ኮፒ እንድሁም ፋይናንሻል ኦርጅናልና ኮፒ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
5. የጨረታ ሰነዱንም በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግና በመለየት በ16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4:30 እስከ 6:30 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው። በ6፡30 የጨረታ ሳጥን ይታሸጋል።
6. ጨረታው በዚሁ ዕለት ከሰዓት 8:30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ፕላንና ልማት ቢሮ በግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ደ/ውስጥ ቢሮ ቁጥር 209 ይከፈታል።
7. የጨረታው አሸናፊ ጨረታውን ማሸነፉን በጽሑፍ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ በ03 የስራ ቀናት ውስጥ ለውል ማስከበሪያ ያሸነፈበትን እያንዳንዱ ሎት ጠቅላላዋ ዋጋ 5% /ሲፒኦ/ በማስያዝ ከፕላንና ልማት ቢሮ ጋር ውል መፈራረም አለበት። ውሉን ከላይ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ቀርቦ ባይፈርም የጨረታ አሸናፊነቱ ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለመንግስት ገቢ ይሆናል።
8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የሲዳማ ብ/ክ/መ/ፕላንና ልማት ቢሮ
