Tender Detail

Tender Details

  • Company የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት
  • Address በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት ከብሩክ ህንፃ ፊት ለፊት ቴሌ አጠገብ ከተሰራው አዲሱ የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ህንፃ ውስጥ 1ኛ ፎቅ ወደ ቀኝ ሲታጠፉ የወልቂጤ ከተማ ፋይናንስ ፅ/ቤት ፡ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0113301548
  • Website
  • Deadline21 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2026-01-21 00:00:00
  • Categories Construction Works

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የከተማው ማዘጋጃ ቤት ህንፃ ማስፋፊያ ግንባታ ግዥ ለማድረግ በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ባላቸው ተወዳዳሪዎች በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

የግዥ መለያ ቁጥር-006/2018

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በጉራጌ ዞን የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት የከተማው ማዘጋጃ ቤት ህንፃ ማስፋፊያ ግንባታ ግዥ ለማድረግ በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ በዘርፉ ህጋዊ ፍቃድ ባላቸው ተወዳዳሪዎች በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት፡- ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች በጨረታው እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል።

1.     ተጫራቾች በጨረታው ለመካፈል ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑ ግብር የከፈሉ መሆኑን የሚያሳይ መረጃ (ክሊራንስ) ማቅረብ የሚችሉ።

2.     ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ የሆኑና ስለዚህ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል። እንዲሁም የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN NUMBER/ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

3.     ተጫራቾች በፌዴራል መንግስት የግዥ ስርዓት በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡና e-GP ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ፡፡

4.     ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ የጨረታ ማስከበሪያ በወልቂጤ ከተማ ፋይናንስ ፅ/ቤት ስም ከታወቀ ባንክ የተረጋገጠ ቼክ፤ CPO 60,000 (ስልሳ ሺህ ብር) በማሰራት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

5.     ተጫራቾች የሚወዳደሩበት የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በስራ ሰዓት ከወ/ጤ ከተማ ፋይናንስ ፅ/ቤት ግ/ን/አስ/ ዋና ስራ ሂደት ክፍል ቀርቦ መውሰድ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።

6.     ተወዳዳሪዎች የጨረታ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /ለአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት አየር ላይ የሚውሉ ሲሆን በ16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 የጨረታው ሳጥን ታሽጎ በዚሁ ቀን 8፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

7.     ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ሁለት ኮፒውን በተናጠል ለይቶ በማሸግ በአንድ እናት ፖስታ በማድረግ በስም በታሸገ ኤንቨሎፕ አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

8.     ተወዳዳሪዎች ከአደራጅ መ/ቤታቸው ሁሉንም የማህበሩ አባላት LMIS ምዝገባ ማድረጋቸው የሚገልፅ ሰርተፍኬት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ ወይም የደረጃ ፍቃድ ማደሳቸውን የሚገልፅ መረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

ማሳሰቢያ

1ኛ/ ማንኛውም ተወዳዳሪ ያቀረበው ዋጋ ከዋጋ ጥናት መረጃ ጋር 15% ከፍ የሚል ከሆነ ውድቅ ይደረጋል።

2ኛ/ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታው ኮሚቴ ጨረታው ሊከፍት ይችላል።

3ኛ/ ከዋጋ ጥናቱ ከ15% በታች በሆነ ዋጋ ጨረታ የሚያሸንፍ ተወዳዳሪ ያለቅድመ ክፍያ ስራ ይጀምራል። እንዲሁም የውል ማስከበሪያ 20% የሚያሲይዝ መሆኑን እንገልፃለን። በተጨማሪም ማስያዣ (ሪቴንሽን) 7% መሆኑን እንገልፃለን።

4ኛ/ በተደረገው የሂሳብ ስህተት ማስተካከያ (Arielmetic Error) የመጣው ጠቅላላ ዋጋ በጨረታ መክፈቻ ስነ- ስርዓት ላይ ከተነበበው ጠቅላላ ዋጋ ከ5% በላይ በሆነ መጠን የሚበልጥ ወይም የሚያንስ ከሆነ የተወዳዳሪው ሰነድ ውድቅ ይደረጋል።

5ኛ/ የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ቀን ከሆነ ቀጣይ ወዳለው የስራ ቀን ይዘዋወራል።

6ኛ/ መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

የወልቂጤ ከተማ አስተዳደር ፋይናንስ ፅ/ቤት

Save Tender