በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ለግብርና ግብዓት ገጠ/ፋ/ዘርፍ የኖራ ግዥ በግልጽ ጨረታ ከዚህ በታች በሰንጠረዥ በተዘረዘረው መሰረት በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የኖራ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ 177/18
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ግብርና ቢሮ ለግብርና ግብዓት ገጠ/ፋ/ዘርፍ የኖራ ግዥ በግልጽ ጨረታ ከዚህ በታች በሰንጠረዥ በተዘረዘረው መሰረት በዘርፉ ከተሰማሩ ድርጅቶች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ተ/ቁ |
የዕቃው አይነት |
መለኪያ |
ብዛት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
የሚታሸግበት ሰዓት |
ሰነዱ የሚገኝበት ቦታ |
|
1 |
ኖራ ከነትራንስፖርቱ እና ጫኝ እና አውራጅን ጨምሮ
|
በኩ/ል
|
15,400
|
100,000
|
በ16ኛው ቀን በ4፡00 ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ይከፈታል |
ደ/ኢ/ግ/ቢሮ ዲላ መምህራን ኮሌጅ ግቢ |
በንግድ ስራ ዘርፉ የታደሰ ፍቃድ ፣የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ፣ የግብርከፋይነት መለያ ቁጥር፣ በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ _ ስለመመዝገባቸውና የቫት መዝጋቢነት ማስረጃዎች ያላቸውና የሚያቀርቡ ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
➢ ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ለ60 ቀናት የፀና መሆን ይኖርበታል፡፡
➢ በተጫራቾች የሚቀርበው የጨረታ ማስከበሪያ ሲ-ፒ-አ ወይም በሁኔታ ላይያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ያሲያዙበትን ማቅረብ አለባቸው፡፡
➢ ተጫራቾች በቢሮ የተዘጋጀውን መደበኛ የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባለው ተከታታይ እስከ 15ኛ ቀን 11፡30 ድረስ የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመከፈል በዲላ ከተማ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ መምህራን ኮሌጅ ግቢ ከሚገኘው የግብርና ቢሮ ግዥ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ከፍል መውሰድ ይችላሉ፡፡
➢ ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነድ በመሙላት ይህ የጨረታ የቴክኒካልና ፋይናሻል አንድ ኦርጅናልና አንድ ኮፒ የማጫረቻ ሰነዶች በአንድነት ፖስታ በማዘጋጀት በ 16 ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት በቢሮ ግዥ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ለዚሁ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይቻላል፡፡ እንዲሁም የጨረታው ሳጥን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዕለቱ 4፡ 30 ተጫራቾች (ተወካዮቻቸው) በተገኙበት በቢሮው የግዥ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ከፍል ይከፈታል፡፡
➢ ቢሮው በቀረበው ጨረታ ላይ ካሸናፊው ድርጅት ጋር ውል ከመፈራረሙ በፊት የግዥውን 20% ፐርሰንት መቀነስ ወይም መጨመር ይችላል፡፡
➢ የጨረታው ሳጥን መከፈቻ በ16ኛው ቀን የመንግስት የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው በቀጣይ ባለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓትና ቦታ የሚከፈት ይሆናል፡፡
➢ ሁለት ተወዳዳሪዎች ያቀረቡት ዋጋቸው እኩል በሚሆንበት ወቅት በእጣ የሚለይ ይሆናል፡፡
➢ ቢሮው ለዚሁ ጨረታ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰርዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
➢ ተጫራቾች ለሚጫረቱት እቃ ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- 046-131-0134 ይጠቀሙ፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ግብርና ቢሮ
