በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደቡብ አዲስ አበባ ሪጅን አይሲቲ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደቡብ አዲስ አበባ ሪጅን ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር ደ/አ/አ/ሪ/ግ/ጨ/002/2018
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደቡብ አዲስ አበባ ሪጅን አይሲቲ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የዕቃው ዓይነት |
የመዝጊያ ቀን እና ሰዓት |
የመክፈቻ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታ ማስከበሪያ |
|
1 |
አይሲቲ እቃዎች እና ቶነሮች |
ጥር 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት |
ጥር 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት |
50,000.00 |
1. ማንኛውም በዘርፉ የተሰማራ የዘመኑን ግብር የተከፈለበት የንግድ ፈቃድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው በጨረታው መሳተፍ ይችላል።
2. ተጫራቾች የመንግሥት ድርጅቶች በሚያወጡት ጨረታ ላይ ለመሳተፍ እንዲችሉ በግዥ ኤጀንሲ ዌብሳይት ላይ የተመዘገቡ መሆኑን ማረጋገጫ ማቅረብ አለባቸው።
3. ተጫራቾች ለጨረታው ዝርዝር ሁኔታዎችን የሚገልጸውን ለሚወዳደሩበት የጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000173799946 (EEU-Southern Addis Ababa Region Customer Contribution) በማስገባት እና ደረሰኙን ይዞ በመምጣት ዘወትር በሥራ ሰዓት ቅዳሜን አስከ 6፡00 ሰዓት ጨምሮ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።
4. አድራሻ- የቀድሞ ግሎባል ሆቴል ፊት ለፊት ማግባንዝ ህንጻ ላይ በሚገኘው ኢ/ኤ/አ /ደቡብ አዲስ አበባ ሪጅን 6ኛ ፎቅ ሰፕላይ ቼይን ንብረት እና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ።
5. ተጫራቾች ለጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ የሚያቀርቡት በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /CPO/ ወይም በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (Bid Bond) ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ኦሪጅናል እና ኮፒ በማለት በተለያየ ፖስታ በማሸግ እና ሁለቱን በአንድ ትልቅ ፖስታ በማድረግ ጨረታ ቁጥር ደ/አ/አ/ሪ/ግ/ጨ/002/2018 የሚል ምልክት በማድረግ ሎቱን በመግለጽ እስከ ጥር 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ድረስ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ፡ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
7. ጨረታው ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ተዘግቶ በተመሳሳይ ቀን ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
8. ተቋሙ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
9. ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር +251-11 470 5377 መደወል ይችላሉ።
በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የደቡብ አዲስ አበባ ሪጅን ጽ/ቤት
