በሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ የአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል የአዳሬ ሆስፒታል B+G+8 ሕንፃን ሊፍት/አሳንሰር ሥራ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
በሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ የአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል የአዳሬ ሆስፒታል B+G+8 ሕንፃን ሊፍት/አሳንሰር ሥራ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ተፈላጊ መመዘኛዎችን የሚያሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች በጨረታው እንዲሳተፉ ይጋበዛሉ፡፡
1. በኤሌክትሮ መካኒካል (Electro-Mechanical) ሥራ ተቋራጭ ደረጃ- 1
2. ተጫራቾች በሥራው መስክ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ (Trade Li-cense) ያላቸው መሆን እና ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
3. በታክስ እና በVAT የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡
4. የታከስ ከፍያ ክሊራንስ ማስረጃ (Tax Clearance) ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. የአቅራቢነት ምስክር ወረቀት ማቅረብ አለባቸው፡፡
6. የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት (Certificate of Registration) ማቅረብ አለባቸው፡፡
7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Security) ብር 500,000.00 (አምስት መቶ ሺህ ብር) በCPO ወይም በባንክ የተመሰከረለት ጋራንቲ ወይንም ቢድ ቦንድ (Bid-bond) ከጨረታ ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
8. የጨረታ ሰነድ ከአዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል ቢሮ ግዢና ክፍያ ፋይናንስ ክፍል በመገኘት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 15 ቀናት/ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 1,000 (አንድ ሺህ ብር ብቻ) በመክፈል መግዛት ይቻላል።
9. የጨረታ ሰነዱ በሰም ለየብቻቸው በታሸገ ኤንቨሎፕ ቴክኒካል አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ እና ፋይናንሻል አንድ ኦርጅናል እና ሁለት ኮፒ በድምሩ ስድስት ፖስታ ወይንም ኤንቨሎፕ ሁሉም ላይ ፊርማና የድርጅቱ ማሕተም የተደረገበት በመያዝ አዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል ግዢና ክፍያ ፋይናንስ ክፍል ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡
10. ጨረታው በዚሁ ቀን 8፡00 ሰዓት ታሽጎ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሆነ ባልተገኙበት አዳሬ አጠቃላይሆስፒታል ግዢና ከፍያ ፋይናንስ ከፍል ይከፈታል፡፡ ይህ ቀን ቅዳሜና እሁድ ከሆነ ሰኞ እንዲሁም በበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
11. በጨረታ አከፋፈት ስነ-ስርዓት የተነበበው ዋጋ እና በአርትሜትከ ቼክበሚደረግበት ጊዜ በሁለቱም መካከል ከ2% በላይ ሆነ በታች ልዩነት ካለ በቀጥታ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል፡፡
12. በጨረታ ላይ ባለው ጠቅላላ ዋጋ ከ10% በላይ የዋጋ ቅናሽ (Rebate) የተደረገ ከሆነ በቀጥታ ከጨረታ ውጪ ይደረጋል፡፡
13. ተጫራቹ ከምህንድስና ግምት 15% በታችና እና በላይ ያቀረበ ከሆነ ከጨረታ ውጪ ይሆናል፡፡
14. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ
ስልክ: 046-220-82-02 / 046-220-45-66
አዳሬ አጠቃላይ ሆስፒታል፣ ሀዋሳ
