Tender Detail

Tender Details

  • Company Ethiopian Petroleum Supply Enterprise(EPSE) (የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት)
  • Address ከሜክሲኮ አደባባይ ወደ ሳርቤት በሚወስደው መንገድ 300 ሜትር ዝቅ ብሎ ፡ አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0115512938
  • Websitehttps://epse.gov.et/
  • Deadline03 Feb 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Security40,000.00 (አርባ ሺህ ብር)
  • opening date2026-02-03 00:00:00
  • Categories Printed Advertising Materials , Printing And Publishing

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የህትመት ውጤቶች ማሰራት ይፈልጋል።

Ethiopian Petroleum Supply Enterprise(EPSE) (የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት)


 

ጨረታ ቁጥር 14/2018

 

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የህትመት ውጤቶች ማሰራት ይፈልጋል።

  1. አጀንዳ የ2019 (2026/2027)
  2. ካሌንደር የ2019 (2026/2027)
  3. የመልካም ምኞት መግለጫ ካርድ (Greeting Card) የ2019 (2026/2027)

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች ማሟላት የሚችሉ ድርጅቶች መወዳደር ይችላሉ፡፡

  1. በጨረታው ለመካፈል በዘርፉ ህጋዊ የሆነ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት (TIN NO) ያላቸው፡፡
  2. የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባወጣው የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀትና ጨረታ ላይ እንዲሳተፉ ከሀገር ውስጥ ገቢ መ/ቤት የሚሰጣቸውን የድጋፍ ደብዳቤ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  3. በተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ግብር ከፋይነት የተመዘገቡና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቶች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከድርጅቱ ግዥ ከፍል ቢሮ ቁጥር 011 መውሰድ ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) ብር 40,000.00 (አርባ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  6. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ እስከ 26/5/2018 ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 602 ለዚህ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  7. ጨረታው በዚሁ ቀን 26/5/2018 ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 4፡05 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት በቢሮ ቁጥር 602 ይከፈታል፡፡
  8. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው

አድራሻ፡- ሜክሲኮ አደባባይ ወደ ሳርቤት በሚወስደው መንገድ 300 ሜትር ዝቅ ብሎ

ስልክ ቁጥር - 011-551-32-88

ፖ.ሣ.ቁጥር 3375 አአ

 

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት

Save Tender