በን/ስ/ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ 06 አስተዳደር ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ አልባሳትና ቁሳቁሶች አወዳደሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በን/ስ/ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ 06 አስተዳደር ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 01/2018
በን/ስ/ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ 06 አስተዳደር ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ አልባሳትና ቁሳቁሶች አወዳደሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ዋጋው በአንድ ላይ በጥቅል በመሙላት የሚወዳደሩ ሲሆን የመነሻ ዋጋ 169774 (አንድ መቶ ስልሳ ዘጠኝ ሺህ ሰባት መቶ ሰባ አራት ብር) ተጫራቾች ይህንን ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጨረታ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለተከታታይ 5 የሥራ ቀናት የጨረታ ሰነድ ከወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት ቀርበው 200 ብር (ሁለት መቶ ብር) መግዛት ይችላሉ፡፡
ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶቹን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት አንስቶ ለ5 የሥራ ቀናት ቄራ ጎፋ ገብርኤል 100 ሜትር ገባ ብሎ በወረዳው 06 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ንብረቶቹን በዝርዝር ወረዳ 06 አስተዳዳር ደንብ ማስከበር ዕቃ መጋዝን ውስጥ ይገኛል፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ በ6 ቀናት ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት ታሽጎ ወዲያው 3፡30 ሰዓት ሳጥኑ ይከፈታል። ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ 5,000 (አምስት ሺህ ብር) ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዛችሁ ማቅረብ አለባችሁ፡፡ አሸናፊው ድርጅት ውጤቱ ከተገለፀበት ቀን አንስቶ በተከታታይ በ3 ቀናት ውስጥ ክፍያውን በፋይናንስ ሂሳብ ቁጥር ክፍያ በመፈጸም ዕቃውን ካላነሳ ያስያዘው ሲፒኦ ተወርሶ ሁለተኛ ለወጣው ይሰጣል፡፡ ጽ/ቤቱ ጨረታው በከፊል ሆነ በውሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በ/ን/ስ/ላ/ክ/ከ/የወ 06 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት
