Tender Detail

Tender Details

  • Company South Ethiopia Regional State Water, Mines And Energy Bureau (በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ ማዕድን ኢነርጂ ቢሮ)
  • Address ዲላ ከተማ : ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0461310241
  • Websitehttps://www.serwmeb.gov.et
  • Deadline19 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Security50,000.00 /ሃምሳ ሺ ብር/ ብቻ
  • opening date2026-01-19 00:00:00
  • Categories Chemicals And Reagents , Health Care, Medical Industry , Laboratory Equipment And Chemicals

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ውሃና ኢነርጂ ቢሮ በኮ ዋሽ ፕሮግራም በጀት ከዚህ በታች የተገለጸውን የውሃ ጥራት መመርመሪያና ማከሚያ ኬሚካሎችና ተያያዥ ህጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡

South Ethiopia Regional State Water, Mines And Energy Bureau (በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ውሃ ማዕድን ኢነርጂ ቢሮ)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር ደ/ኢ/ውሃ/ጥ/መ/ኬ/ ግዥ/005/2018

 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ውሃና ኢነርጂ ቢሮ በኮ ዋሽ ፕሮግራም በጀት ከዚህ በታች የተገለጸውን የውሃ ጥራት መመርመሪያና ማከሚያ ኬሚካሎችና ተያያዥ ህጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልፅ ጨረታ መግዛት ይፈልጋል፡፡

  • ሎት 1 የውሃ ጥራት መመርመሪያና ማከሚያ ኬሚካሎችና ተያያዥ ዕቃዎች ግዥ

ከዚህ በላይ ለተገለፁት እቃዎች በውድድር ለመሳተፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች

  1. በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፍቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው፤
  2. ተጫራቾች ዋጋቸውን የሚገልፀውን ሠነድ በታሸገ ፖስታ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ እስከ 16ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ድረስ የሚያስገቡና የሚታሸግ ሲሆን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በዕለቱ 9፡00 ሰዓት ይከፈታል፤
  3. ይህ እንዳለ ሆኖ 16ኛው ቀን የስራ ቀን በማይሆንበት ጊዜ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ጊዜና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፤
  4. ከላይ ከሎት 1 የተገለጸው የጠቅላላ ሽያጭ ዋጋ ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ/ በላይ ሲሆን የቫት ተመዝጋቢዎች ብቻ መጫረት የሚችሉ መሆኑን፤
  5. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለ90 ቀን ፀንቶ የሚቆይ ብር 50,000.00 /ሃምሳ ሺ/ ብቻ በሲፒኦ ወይም እንኮንድሽናል ባንክ ጋራንቲ ማቅረብ አለባቸው፤
  6. ጨረታው ለሶስት ወራት 90 (ዘጠና) ቀናት ብቻ ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል፤
  7. አሸናፈው ተጫራች የውሃ ጥራት መመርመሪያና ማከሚያ ኬሚካሎችና ተያያዥ ዕቃዎችን ግዥ የከልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ባወጣው የግዥ አፈፃፀም መመሪያና ጠቅላላ የውል ሁኔታዎች መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፤
  8. የጨረታ ሰነዱን ሎት የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ/ በመክፈል ከግዥ ንብረት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ቢሮ መግዛት ይቻላል፤
  9. ተጫራቾች በጨረታ በሎት በቀረበው ድምር ዋጋ ላይ ከ3% በመብለጥም ሆነ በማነስም የቀረበ ድምርስህተት ከጨረታ ውጪ ያደርጋል፤
  10. ቢሮው ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፤
  11. ተጫራቾች የፋይናንሻልና የቴክኒከ መገምገሚያ መስፈርት በመሙላትና በተለያየ ሁለት ፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የፋይናንሻልና የቴክኒካል መሆኑን በመግለጽ ፋይናሻል እና ቴክኒካል ሁለት ሁለት ኮፒ ጋር በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

ማሳሰቢያ፡-

ሽያጩ ቫትን ጨምሮ ከብር 20,000.00 /ሃያ ሺ/ በላይ ከሆነ ከቫት ተመዝጋቢዎች ላይ የቫቱን 50% ቀንሰን የምናስቀር መሆኑን አንገልፃለን፡፡

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0461310241 ደውለው ይጠይቁ

አድራሻ፡- ደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ውሃና ኢነርጂ ቢሮ

 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ውሃና ኢነርጂ ቢሮ

 

Save Tender