በኦሮሚያ ብሔራዊክልላዊመንግስትየኦሮሚያኢንቨስትመንትእናኢንዱስትሪ ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት የቢሮውን አገልግሎት ለማዘመን የሶፍትዌር ልማት (Software Development) ለማሠራት ይፈልጋል በመሆኑም የሶፍትዌር አልሚ ድርጅቶች አጫርቶ ሶፍትዌር ማስለማት ይፈልጋል።
Oromia Investment and Industry Bureau (የኦሮሚያ ኢንቨስትመንት እና ኢንዱስትሪ ቢሮ)
የጨረታ ማስታወቂያ
በኦሮሚያ ብሔራዊክልላዊመንግስትየኦሮሚያኢንቨስትመንትእናኢንዱስትሪ ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት የቢሮውን አገልግሎት ለማዘመን የሶፍትዌር ልማት (Software Development) ለማሠራት ይፈልጋል በመሆኑም የሶፍትዌር አልሚ ድርጅቶች አጫርቶ ሶፍትዌር ማስለማት ይፈልጋል።
ስለዚህ የሚከተለውን የጨረታመስፈርት የሚያሟሉ ተጫራቾች እንዲወዳደሩ ተጋብዘዋል።
- ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑ ግብር የከፈሉ እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ / VAT/ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቹ በባለፉት 3 (ሦስት) ተከታታይ ዓመታት በእያንዳንዱ ዓመት ቢያንስ 4,000,000 ብር የዓመታዊ አማካይ ሽያጭ መጠን መኖር አለበት። ይህ ማለት በአጠቃላይ ቢያንስ 12,000,000 ብር የሦስት ዓመት ሽያጭ መኖር አለበት። ፍቃድ ባለው ኦዲተር የተረጋገጡ የፋይናንስ ሪፖርቶች መቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቹ ድርጅት በሶፍትዌር ልማት ዘርፍ ቢያንስ 6 (ስድስት) ዓመት እና ከዚያ በላይ ልምድ ያለው መሆን አለበት።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና አጠቃላይ የሚያቀርቡትን የፋይናንስ ጥቅል ዋጋ 2% (ሁለት በመቶ) በባንክ በተመሰከረለት /CPO/ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘው የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት ወደ ቄራ በሚወስደው መንገድ ሣር ቤት የሚገኘው በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የኦሮሚያ ኢንቨስትመንት እና ኢንዱስትሪ ቢሮ 1ኛ ፎቅ በመቅረብ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር /በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን በሁለት የተለያዩ ፖስታ በማሸግ ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀ የጨረታ ሣጥን ውስጥ እስከ 10ኛው ቀን 4:30 ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ከቆየ በኋላ በ10ኛው ቀን ከጠዋቱ 4:30 ታሽጎ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በኦሮሚያ ኢንቨስትመንት እና ኢንዱስትሪ ቢሮ 5:00 ሰዓት ይከፈታል በዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታው ይከፈታል።
- ቢሮው የሚያሠራውን ሥራ 20% የጨመርም ሆነ የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች ሥራውን በተባለው ጊዜ ውስጥ አጠናቀው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
አድራሻ፡- በኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሣር ቤት በሚገኘው ህንፃ 1ኛ ፎቅ
ለተጨማሪ ማብሪሪያ፦ በስልክ ቁጥር 0911 631 348 / 0913 152 039 / 0917 805 333 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
የኦሮሚያ ኢንቨስትመንት እና ኢንዱስትሪ ቢሮ
