በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት የካፋ ዞን ዴቻ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለዴቻ ወረዳ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት የንፁህ መጠጥ ውሃ ምንጭ ግንባታንና ጥገናን በየሎት በመከፋፈል ማስገንባትና ማስጠገን ይፈልጋል።
በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መ/ ካፋ ዞን ዴቻ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት አውራዳ
የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መንግስት የካፋ ዞን ዴቻ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለዴቻ ወረዳ ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት የንፁህ መጠጥ ውሃ ምንጭ ግንባታንና ጥገናን በየሎት በመከፋፈል ማስገንባትና ማስጠገን ስለሚፈልግ አዲስ ግንባታ የሚገነባ በየፓኬጅ በዬባ፤ በመልጋዋና በሾንጋ ቀበሌዎች ሲሆኑ ጥገና የሚካሄድበት በዮካ ቀበሌ በጋለ ጎጆ ጎጥ ላይ ቀደም ሲል የተገነባው አጠቃላይ የውሃ ግንባታ ሥራ የተበላሸውን ሙሉ ጥገና ሥራ ለማሰራት በGC/WC ደረጃ 5/6 እና ከዛ በላይ የግንባታ ፍቃድ ያላቸውን ተቋራጮችን በጨረታ አወዳድሮ በፓኬጅ እና በየሎት ለማስገንባት ይፈልጋል፡፡
- ለሎት 01 አዲስ ግንባታ ደረጃ 5 GC/WC እና ከዚያ በላይ የግንባታ - ፍቃድ ያለው ለሦስቱ ቀበሌ በዬባ፤ በመልጋዋና በሾንጋ ማስገንባት ሲሆን
- ለሎት 02 ጥገና ደረጃ 6 GC/WC እና ከዚያ በላይ የግንባታ ፍቃድ ያለው በዮካ ቀበሌ በጋለ ጎጆ ጎጥ ማስጠገን ሲሆን በዚህም መሰረት፡-
- ተጫራቾች ደረጃ 5 /6/ GC/WC እና ከዚያም በላይ የግንባታ ፈቃድ ያለው:- በ2017/18 /ዓ/ም የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የተ.እ.ታ (ቫት) ምዝገባ ም/ወረቀት፣ የግብር ከፋይ መለያ (TIN) ም/ወረቀት እንዲሁም በመንግስት ግዥ በGC/WC ግንባታ ስራ በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ ሁሉ በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡ በ2016/2017 ዓ/ም በጥራት ሰርቶ ስላስረከቡት በውሃ ሥራ ብቻ/ GC/WC /ግንባታ የመልካም ስራ አፈጻጸም ደብዳቤ ወይም የምስክር ወረቀት ያለው፣ በተጨማሪ ክፍያ የተፈጸመበትን የቫት ደረሰኝ ማቅረብ የሚችል በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት በሥራ ሰዓት ብቻ ለሎት 01 እስከ 21ኛው ቀን ድረስ ለወረዳው ገቢዎች ጽ/ቤት በየፓኬጁ ሆኖ ለእያንዳንዱ ቀበሌ የማይመለስ 300.00 ብር በፊደል /ሦስት መቶ ብር ብቻ/ ጠቅላላ ለ3ቱ ቀበሌዎች 900 /ዘጠኝ መቶ ብር ብቻ/ በመክፈል ከመ/ቤታችን ግዥ ኬዝ ቲም ሰነድ በመውሰድና በዝርዝሩ መሰረት ዋጋ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት በሥራ ሰዓት ብቻ ለሎት 02 እስከ 22ኛው ቀን ድረስ ለወረዳው ገቢዎች ጽ/ቤት ለጥገና የማይመለስ 300.00 ብር /ሦስት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከመ/ቤታችን ግዥ ኬዝ ቲም ሰነድ በመውሰድና በዝርዝሩ መሰረት ዋጋ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በመውሰድ ከተ.እ.ታ /ቫት/ ጋር በመሙላት እንዲሁም ከላይ የተዘረዘሩትን የንግድ ፈቃድና ተያያዥ የመረጃ ኮፒዎችንና የጨረታ ማስከበሪያ /CPO/ በአንድ ፖስታ በማሸግ፣ ዋጋ የተሞላበትን ኦርጂናል የጨረታ ሰነድ በሌላ ፖስታ በማሸግ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሚቆጠሩ ተከታታይ ቀናት ለሎት 01 እስከ 21ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ለሎት 02 22ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ለዚሁ ጉዳይ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዕለቱ 8፡30 ላይ ይከፈታል፡፡ እለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ሠዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 01. ብር 30,000 /ሰላሣ ሺህ ብር/ ብቻ በባንክ በተመሰከረ የክፍያ ማዘዣ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለሎት 02 ብር 20,000 /ሃያ ሺህ ብር ብቻ/ በባንክ በተመሰከረ የከፍያ ማዘዣ (CPO) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታ አከፋፈት ወቅት የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን አከፋፈት ሂደት አያስተጓጉለውም፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 094592714 ደውለው መረዳት ይችላሉ፡፡
በደ/ም/ሕ/ክ/መ/ካፋ ዞን የዴቻ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት/ አውራዳ
