Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ የደብረብርሃን ቅ/ፅ/ቤት
  • Address ደብረብርሃን : አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 0116375030
  • Website
  • Deadline14 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Securityየመንገድ ሥራውን ጠቅላላ ዋጋ 2% ቫትን አካቶ ነው የመንገድ ማሰሪያ ዋጋ ከብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ኢንተርፕራይዙ Withholding tax /3%/ የሚሰበስብ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  • opening date2026-01-14 00:00:00
  • Categories Road And Bridge Construction , Agricultural

በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ የደብረ ብርሃን ቅ/ጽ/ቤት ለደን ምርት ማውጫ አዲስ መንገድ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡

በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ የደብረብርሃን ቅ/ፅ/ቤት


 

ለኤክስካቫተር ማሽን ኪራይ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ የደብረ ብርሃን ቅ/ጽ/ቤት ለደን ምርት ማውጫ አዲስ መንገድ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማሠራት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ተጫራቾች፡-

  1. በዘርፉ የተሰማሩ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin/ ያላቸውና የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሱትንና ሌሎች የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  3. በጨረታው የሚቀርበውን የመንገድ ሥራ ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
  4. የጨረታ ሰነዱን በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የሥራ ቀናት ውስጥ /ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ/ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ለእያንዳንዱ ጨረታ ሰነድ በመክፈል በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ደብረ ብርሃን ቅ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 3 መግዛት ይችላሉ፡፡
  5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የመንገድ ሥራውን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ ትእዛዝ /cpo/ ማስያዝ አለባቸው፡፡
  6. የጨረታ ማስከበሪያ 2% የሚያሲዙት ቫትን አካቶ ነው፤ የመንገድ ማሰሪያ ዋጋ ከብር 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ኢንተርፕራይዙ Withholding tax /3%/ የሚሰበስብ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ዋጋውን በኦርጅናል ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የሚያቀርቡበትን ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ፤ ስምና አድራሻቸውን በመጻፍ ፈርመው ማህተም በማድረግ የጨረታ ፖስታውን በማሸግ በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ደብረ ብርሃን ቅ/ጽ/ቤት የመንገድ ሥራ (የኤክስካቫተር ማሽን ኪራይ) ግልጽ ጨረታ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የሥራ ቀናት ውስጥ /ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ/ እስከ መጨረሻው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት 4፡00 ሰዓት ላይ ሳጥኑ ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት /ባይገኙም/ ይከፈታል፡፡
  8. ተጫራቾች የሚጫረቱበት ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ ተእታ 15% ጨምሮ ነው፡፡
  9. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ውድድሩ በጥቅል ዋጋ መሞላት አለበት፡፡

 

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0116 37 50 30 / 0932 49 71 18

 

በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ የደብረ ብርሃን ቅ/ጽ/ቤት

 

Save Tender