Tender Detail

Tender Details

  • Company በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አራት ኪሎ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል
  • Address , Phone: 0111261365
  • Website
  • Deadline05 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Security3,000
  • opening date2026-01-05 00:00:00
  • Categories Sport Materials And Sportswear , Equipment

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አራት ኪሎ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል ያገለገሉ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አራት ኪሎ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል


የአራት ኪሎ ስፖርት፣ትምህርትና ስልጠና ማዕከል

ያገለገሉ ዕቃዎች የሽያጭ ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 03/2018 ዓ.ም

ያገለገሉ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

የተጫራቾች መመሪያ

በጨረታው ለመሳተፍ የሚችሉ ተጫራቾች፡-

  1. ለመጫረት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራቾች በስራ መስክ የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸውን ህጋዊ በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማስረጃ መቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  2. የዋጋ ማቅረቢያ ሲሞላ ስርዝ ድልዝ እንዲኖር አይፈለግም ፡፡ ሰነዱ ስርዝ ድልዝ ካለው ከጨረታው ውጪ ይሆናል፡፡
  3. ተጫራቾች መ/ቤቱ ያዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ዝርዝር ያየዘው መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡ ዋጋ ሲሞላ የተጫራቹ ሙሉ ስም፣ፊርማ፣ማህተም ያረፈበት፣አድራሻ፣ ክፍለ ከተማ፣የቤት ቁጥርና የስልክ ቁጥራቸውን መግለፅ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. ተጫራቾች መ/ቤቱ ያዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከአራት ኪሎ ስፖ/ትም/ስል/ማዕከል የፋይ/ግዥ ንብ/አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 8 በመምጣት በ200 ብር /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመግዛት መውሰድ ይችላሉ፡፡
  5. ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 7/ሰበት/ የስራ ቀናት ውስጥ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን፣ ጨረታውን በ7ኛው ቀን ከቀኑ 9፡30 ሰዓት ላይ የሚያበቃና ሳጥኑም ታሽጎ በ7ኛው ከቀን 10፡00 ሰዓት ላይ በማዕከሉ አዳራሽ ቁጥር 10 በግልፅ የሚከፈት ይሆናል፡፡
  6. ተጫራቾች ጨረታው በሚከፈትበት ዕለት ድርጅቱን የሚገልፅ ህጋዊ መታወቂያና ውክልናን የሚገልፅ ደብዳቤ በመያዝ ጨረታው ሲከፈት መከታተል ይችላሉ፡፡
  7. ተጫራቾች የገዙትን የጨረታ ሰነድ አየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ 7 /ሰበት/ የስራ ቀናት ውስጥ የታሸገ ፖስታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ፋይ/ግዥ/ንብ/ አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 9 ሰነዱን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች መ/ቤቱ ያዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ዝርዝር ያየዘው የአንዱ ዋጋ መሟላት አለበት፡፡
  9. መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  10. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያገልግል የመጫረቻ ዋጋ ላይ ሲፒኦ (CPO) ብር 3,000/ ሶስት ሺህ ብር/ በባንከ የተረጋገጠ ከጨረታ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

አድራሻ፡- አራት ኪሎ ስፖርት፤ ትምህርትና ስልጠና ማዕከል ቢሮ ቁጥር 8 የመንግስት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና ኤጀንሲ መስሪያ ቤት ፊት ለፊት

ለበለጠ መረጃ ስልክ 0111 261 365

ማሣሰቢያ፡-ያገለገሉ ንብረቶችን መምረጥና ይህንን አልወስድም ማለት የማይቻል መሆኑን ከወዲሁ እናሳስባለን።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አራት ኪሎ ስፖርት ትምህርትና ስልጠና ማዕከል

Save Tender