Tender Detail

Tender Details


በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የአብክመ ጤና ቢሮ የደቡብ ወሎ ዞን የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውል ለ2018 ዓም በጀት ዓመት መድኃኒት ሪኤጀንት ሰፕላይ የሕክምና መሣሪያ ጥገና ለ6 ወር ፤ የጥበቃ አገልግሎት ለ1 ዓመት የሚያገለግል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት/ለማሠራት ይፈልጋል፡፡

የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል


 

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የአብክመ ጤና ቢሮ የደቡብ ወሎ ዞን የደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውል ለ2018 ዓም በጀት ዓመት መድኃኒት ሪኤጀንት ሰፕላይ የሕክምና መሣሪያ ጥገና ለ6 ወር ፤ የጥበቃ አገልግሎት ለ1 ዓመት የሚያገለግል በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት/ለማሠራት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም አግባብነት ያለቸውን ሁሉ በጨረታው እየጋበዝን

  1. ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የአቅርቦትና የአገልግሎት አይነት የተዛመደ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችሉ
  4. የግዥው ወይም የአገልግሎቱ መጠን ከ200,000.00 በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ የሆነ
  5. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር ከነ-4 የተገለፁትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከጨረታው ኦርጅናል ሰነዶች ጋር ማቅረብ ይጠበቃል
  6. ተጫራች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የሥራ ቀናት ከሆስፒታሉ ግዥ ከፍል የማይመለስ 300 ብር በመክፈል ማግኘት ይችላሉ
  7. ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ከሚያቀርቡት ጠቅላላ ዋጋ 2% ሲፒኦ እና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በማስያዝ ከኦርጅናሉ የጨረታ ሰነድ ጋር ማያያዝ ይኖርባቸዋል ጨረታ በሚያስገቡበት ጊዜ ዋናው የጨረታ ሰነድ እና ኮፒውን ለብቻው በፖስታ በማሸግ እንደገና ሁለቱንም በአንድ ላይ በትልቅ ፖስታ በጥንቃቄ በሰም በማሸግ የድርጅቱ ስም አድራሻውና ማህተም በመምታት የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል. በመሆኑም ከላይ የተዘረዘሩትን ካላሟሉ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  8. የጨረታው ተሳታፊዎች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በማስታወቂያ በወጣበት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት በመጨረሻ በ16ኛ የሥራ ቀን ከረፋዱ 4፡00 ታሽጎ በዕለቱ 4፡30 ይከፈታል፡፡
  9. ሆስፒታሉ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  10. ሆስፒታሉ ቫት (7.5) እና ዊዝ ሆልድ 3% ቆርጦ የሚያስቀር መሆኑን፡፡
  11. ሆስፒታሉ በሚጋብዘው የቴክኒክ ባለሙያ ተረጋግጦ እቃው /አገልግሎቱ /ገቢ ይሆናል፡፡
  12. አስፈላጊ መረጃ መስጠት ከፈለጉ በሆስፒታሉ ስልከ ቁጥር 0331117670 መደወል ይችላሉ፡፡

 

ደሴ አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

Save Tender