Tender Detail

Tender Details

  • Company The Brooke Hospital for Animals. (ዘ ብሩክ ሆስፒታል ፎር አኒማልስ)
  • Address 22 ማዞሪያ በአውራሪስ ከቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል በጀርባ ባለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል ወደ 24 በሚወስደው መንገድ ላይ በንጋት ህንፃ እና በአዳነ ገብሩ ህንፃ በኩል ወደ ውስጥ ገባ ብሎ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-661-00-69
  • Websitehttps://www.thebrooke.org/
  • Deadline09 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Securityከጠቅላላው የጨረታ ዋጋቸው 2%
  • opening date2026-01-09 00:00:00
  • Categories Road And Bridge Construction , Building Construction

ዘ ብሩክ ሆስፒታል ፎር አኒማልስ በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በቁጥር፡ 0883 የተመዘገበ መንግስታዊ ያልሆነ ግብረሰናይ ድርጅት ሲሆን በዚህ ዓመት ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ዘንዘልማ በሚገኘው የእንስሳት ህክምና ፋኩሊቲ የእንስሳት ጤና እንክብካቤ ፣ የህክምና መስጫ ማዕከል ውስጥ የእግረኛ መንገድ /Walk way/፣ የእንሰሳት ለይቶ ማቆያ እና የቆሻሻ ማቃጠያ ለመስራት ይፈልጋል።

The Brooke Hospital for Animals. (ዘ ብሩክ ሆስፒታል ፎር አኒማልስ)


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

ዘ ብሩክ ሆስፒታል ፎር አኒማልስ በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን በቁጥር፡ 0883 የተመዘገበ መንግስታዊ ያልሆነ ግብረሰናይ ድርጅት ሲሆን ከተመዘገበበት ጊዜ ጀምሮ ዋና ቢሮውን አዲስ አበባ በማድረግ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡ የድርጅቱ አላማ የጋማ እንስሳትን ደህንነትና ጤንነት ማሻሻል እና በእነዚህ የጋማ እንስሳት ጉልበት ኑሯቸውን የመሰረቱ የማህበረሰብ ክፍሎችን የኑሮ ሁኔታ ማሻሻል ሲሆን ይህንንም ለመተግበር ከመንግስት የእንስሳት እና የግብርና ተቋማት ጋር በትብብር ይሠራል፡፡

ድርጅታችን በዚህ ዓመት ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ዘንዘልማ በሚገኘው የእንስሳት ህክምና ፋኩሊቲ የእንስሳት ጤና እንክብካቤ ፣ የህክምና መስጫ ማዕከል ውስጥ የእግረኛ መንገድ /Walk way/፣ የእንሰሳት ለይቶ ማቆያ እና የቆሻሻ ማቃጠያ ለመስራት እቅድ ይዞ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።

ይህንንም ለማድረግ ድርጅታችን ብሩክ ኢትዮጵያ ብቁ እና መስፈርቶችን የሚያሟሉ ደረጃ ስድስት ጠቅላላ/ህንጻ ስራ ተቋራጭ (GC/BC Six and above) እና ከዚያ በላይ ቀጥሎ ለተዘረዘሩት ሥራዎች የጨረታ ሰነዶችን በታሸገ ኤንቨሎፕ በማቅረብ እንድትወዳዳሩ ይጋብዛል።

 

የጨረታ ቁጥር

የፕሮጀክቱ ስም

ከተማ

የስራው አይነት

ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ

B-ETH/18/2025

Bahir Dar University

Animal Welfare and Health Training Centre Extension Work

Rehabilitation Centre /Stable/, Walk Way and Incinerator

 

    1. ተጫራቾች ህጋዊና የዘመኑ የታደሰ ፈቃድ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (የቫት) ተመዝጋቢ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ያላቸው መሆን አለባቸው፡፡ ማስረጃቹህን የጨረታ ሰነድ ስትገዙ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል።
    2. ተጫራቾች የተሟላ የጨረታ ሰነዱን አዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 የቤት ቁጥር 797 ከሚገኘው የድርጅታችን ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
    3. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከጠቅላላው የጨረታ ዋጋቸው 2% ቦንድ በሲፒኦ መልክብቻ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ሲፒአው የጨረታ ኤንቨሎፕ ውስጥ ለብቻ ታሽጎ መቅረብ አለበት፡፡ የቀረበው ሲፒኦ ከሂሳብ ስሌት ማስተካከያ በኋላ ለሚመጣው ጠቅላላ ዋጋ የ2ቱን ከ20% በታች ከሆነ ተጫራቹ ከውድድር ውጪ ይደረጋል፡፡
    4. ተጫራቹ አሸናፊ ከሆነ ለቅድመ ክፍያ የሚሆን የሁኔታዎች ያልተወሰነ Unconditional Bank Guarantee/ የባንክ ዋስትና 30% ማቅረብ የሚችል መሆን ይጠበቅበታል፡፡
    5. ተጫራቾች የታሸገውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 ቀናት ውስጥ ከላይ በተ.ቁ. 2 በተጠቀሰው አድራሻ በሚገኘው የብሩክ ጽ/ቤት ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታው መዝጊያ ቀንና ሰዓት በ15ኛው ቀን ከቀኑ 7፡30 ሰዓት ሲሆን፤ የጨረታ ማቅረቢያው 15ኛው ቀን ቅዳሜና እሁድ፣ ወይም በበዓል ቀናት ከዋለ የጨረታ መዝጊያው ቀን በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከቀኑ 8፡00 ይሆናል፡፡ ከተጠቀሰው ቀንና ሰዓት ውጭ የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም፡፡
    6. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በተዘጋበት ቀን በተ.ቁ. 5 የተመለከተው መሰረት ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ይከፈታል፡፡
    7. ድርጅቱ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ የጨረታ መክፈቻውን ቀን የማራዘም ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ እንዲሁም ቀደም ብሎ በድርጅቱ ሥራዎች ላይ ዝቅተኛ አፈፃፀም ያላቸውን የጨረታ ተወዳዳሪዎች ከጨረታው እንዳይሳተፉ ማድረግ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

ለበለጠ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር 011-661-0069/011-662-1885 በመደወል ወደም በኢሜይል info@thebrookeethiopia.org አድራሻችን መጠየቅ ይቻላል፡፡

አድራሻችን፣ 22 ማዞሪያ በአውራሪስ ከቅዱስ ገብርኤል ሆስፒታል በጀርባ ባለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል ወደ 24 በሚወስደው መንገድ ላይ በንጋት ህንባ እና በአዳነ ገብሩ ህንፃ በኩል ወደ ውስጥ ገባ ብሎ፡፡ ስልክ 011-661-0069/ 011-662-1885

 

ዘ ብሩክ ሆስፒታል ፎር አኒማልስ

Save Tender