የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሥራና ከህሎት ቢሮ ከኢጣሊያ መንግሥት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በአራት የሥራ ማዕከላት ማለትም በሀንጠጠ፤ ድላሞ አንፋራራ፣ ቴሶ እና ሳሳሞ ዴላ የሥራ ማዕከላት አገልግሎት መስጫ ማዕከላትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል።
የሲዳማ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ
ግልፅ የግንባታ ሥራ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 001BOLS/2018
የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ሥራና ከህሎት ቢሮ ከኢጣሊያ መንግሥት በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በአራት የሥራ ማዕከላት ማለትም በሀንጠጠ፤ ድላሞ አንፋራራ፣ ቴሶ እና ሳሳሞ ዴላ የሥራ ማዕከላት አገልግሎት መስጫ ማዕከላትን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማስገንባት ይፈልጋል።
በዚህም መሰረት የሚከተሉትም መስፈርት የሚያሟሉ GC-5/BC-5 እና ከዘ ዝዚያ በላይ የሆኑ ተጫራቾች ሁሉ መወዳደር የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
ለጨረታ የቀረቡ ሎቶች፡-
|
ሎት |
የፕሮጀክቱ መገኛ |
ፕሮጀክቱ |
ለፕሮጀክቱ የሥራ ማጠናቀቂያ ጊዜ |
የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ጋራንት (ጨረታው ከተከፈተበት ቀን ጀምሮ ለ120 ቀናት የሚያገለግል) |
|
|
ዞን |
ወረዳ |
||||
|
1 |
ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን |
ሎ/አባያ ሀንጣጣ |
ሀንጣጣ ሥራ ማዕከል |
140 ተከታታይ ቀናት |
175,000 |
|
2 |
ደቡባዊ ሲዳማ ዞን |
አ/ጩኮ ቴሶ |
ቴሶ ሥራ ማዕከል |
120 ተከታታይ ቀናት |
98,000 |
|
3 |
ማዕከላዊ ሲዳማ ዞን |
ዳሌ ሳሳሞ |
ሳሳሞ ዴላ ሥራ |
120 ተከታታይ ቀናት |
89,000 |
|
4 |
ሰሜናዊ ሲዳማ ዞን |
ሸበዲኖ ድላሞ አንፋራራ |
ድላሞ አንፋራራ ሥራ ማዕከል |
120 ተከታታይ ቀናት |
105,000 |
ስለሆነም ተጫራቾች ማሟላት ያለባቸው
- በሚወዳደሩበት ዘርፍ በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያላቸው።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ሲ/ብ/ክ/መ/ሥራና ክህሎት ቢሮ ሁለተኛ ህንጻ ቢሮ ቁጥር 01 በአካል በመቅረብ የማይመለስ ብር 1100 /አንድ ሺህ አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን በመውሰድ ለመጫረቻ የሚያስፈልጉ ሰነዶችንና ማስረጃዎችን በማሟላት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ30 ቀናት ክፍት ሆኖ ስለሚቆይ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ የተጠቀሰውንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎችን ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ውድድር ወቅት ቴክኒካል ዋና እና ኮፒ፤ ፋይናንሻል ዋና እና ኮፒ በመለያየት ማቅረብ አለባቸው።
- አንድ ተጫራች ከሁለት ሎት በላይ መወዳደር አይችልም፡፡
- የጨረታ ሰነድ ተሞልቶ ከጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ጋር በፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የሞሎትን ሎት በመግለጽ ኮፒና ዋና በመለያየት በሁለት ፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ30 ቀናት ከቀን 17/04/2018 ዓ.ም ጀምሮ ክፍት ሆኖ ቆይቶ በ31ኛው ቀን ማለትም በ18/05/2018 ዓ.ም ከጠዋት 4፡00 ሰዓት ታሽጎ በዚሁ እለት በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቢሮ አዳራሽ ይከፈታል። ተጫራቾች ባይገኙም ጨረታውን ከመከፈት አያግደውም፡፡
- የጨረታ መክፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓል ቀን ከሆነ ጨረታው በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ስለጨረታው ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ ሲ/ብ/መ/ሥራና ከህሎት ቢሮ በግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ክፍል በግንባር በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር፡- 046211841 ወይም 0462121517 በመደወል ማግኘት ይቻላል።
- ቢሮው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- አድራሻ ሲዳማ ክልል ሀዋሳ ከተማ ሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ጎዳና ሲዳማ ከልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጎን እንገኛለን።
የሲዳማ ክልል ሥራና ክህሎት ቢሮ
ሀዋሳ
