Tender Detail

Tender Details

  • Company የነጆ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address ነጆ ከተማ : በቤንሻንጉል-ጉምዝ ክልል : ኢትዮጵያ, Phone: 09 17 09 37 49
  • Website
  • Deadline21 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price1000.00
  • Bid Security20,000
  • opening date2026-01-21 00:00:00
  • Categories Rent

በምዕራብ ወለጋ ዞን የነጆ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዘመን ለከተማ አስተዳደር መንገድ ሥራ የሚውል ዶዘር ባለሰንሰለት ለ400 ሰዓት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች በተገለጸው መሠረት ተጫራቾች ይህንን ጨረታ እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል።

የነጆ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት


የጨረታ ማስታወቂያ

 

በምዕራብ ወለጋ ዞን የነጆ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዘመን ለከተማ አስተዳደር መንገድ ሥራ የሚውል ዶዘር ባለሰንሰለት ለ400 ሰዓት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመከራየት ስለሚፈልግ ከዚህ በታች በተገለጸው መሠረት ተጫራቾች ይህንን ጨረታ እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል።

በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች፡-

  1. ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ዕቃ ጋር የተዛመደ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን የ2017 ዓ.ም ግብር የከፈሉ።
  2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና ለዚሁም ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  3. በገንዘብና ኢኮኖሚ ሚኒስቴር ወይም በሌላ በሚመለከታቸው ፈቃድ ሰጪ አካላት አቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡና የምስክር ወረቀት ያላቸው።
  4. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታው ሰነድ ላይ የተገለጹትን ማንኛውንም ሁኔታዎች መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይም ጨረታውን ትቻለሁ ማለት አይችልም።
  5. ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል ነጆ ከተማ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ቁጥር 7 ቀርበው መግዛት ይቻላል።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ዋናውንና ፎቶ ኮፒውን በመለየት በታሸገ ፖስታ በነጆ ከተማ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ውስጥ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ማስገባት ይኖርበታል።
  7. ዶዘሩን ጭኖ ነጆ ከተማ አስተዳደር የመቅረብና የመመለስ የአቅራቢው ድርጅት ይሆናል።
  8. ማንኛውም የኦፕሬተር ወጪ፣ ነዳጅ የአቅራቢ ድርጅቱ ይሆናል።
  9. ጨረታው ከታኅሣሥ 18 ቀን 2018. ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥር 13 ቀን 2018 ዓ.ም 3፡30 ሰዓት ቆይቶ የጨረታው ሣጥን ይዘጋል። በዚሁ ዕለት በ4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ነጆ ከተማ አስተዳደር ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 1 ይከፈታል
  10. ማንኛውም ተጫራች በጨረታው ተካፋይ ለመሆን ተመላሽ የሚሆን ብር 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) የጨረታ ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ወይም በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ በተመሰከረለት ቼክ ማስያዝ ይኖርበታል።
  11. ለጨረታው የሚቀርበው ሰነድ ድልዝ የሌለው ሆኖ በጉልህ መጻፍ ይኖርበታል።
  12. በጨረታው ያሸነፈው ተጫራች ለውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይኖርበታል።
  13. በጨረታው ያሸነፈው ተጫራች የጨረታውን ግዴታ ባይወጣ ለውል ማስከበሪያ 10% ያስያዘው ገንዘብ ለጽ/ቤት ገቢ ይሆናል።
  14. ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡።

ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ፡-

ስልክ ቁጥር 09 17 09 37 49፣ 09 22 42 96 65፣ 09 17 29 95 70

 

የነጆ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት

Save Tender