የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ከዚህ በታች የተገለፀውን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
Metehara Sugar Factory (መተሐራ ስኳር ፋብሪካ)
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር MSF/LF/08/2025
የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ከዚህ በታች የተገለፀውን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ጥቅል አንድ ኮስቲክስ ሶዳ (Causts Soda)
ጥቅል ሁለት፡- የአረም ማጥፊያ ኬሚካል (2-4diamin, Herbicide for bread leaved Weed Control,) በመሆኑም ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾችን እንዲወዳደሩ ይጋብዛል፡፡
- ሕጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፤ የዘመኑን የሀገር ውስጥ ገቢ ግብር አጠናቀው የከፈሉና ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶች ለእያንዳንዱ ጥቅል የማይመለስ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ዘወትር በሥራ ሠዓት ሜክሲኮ አደባባይ ፊሊፕስ ህንፃ ግዥ ቡድን 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 215 የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ ገዝተው በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ሲገዙ የንግድ ፈቃድ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት ሠነድ ጋር የታደሰ የንግድ ፈቃድ የአቅራቢዎች የምዝገባ ሠርተፍኬት እና ለጨረታ ማስከበሪያ የጠቅላላ ዋጋውን ከ1.5 - 2% የሚሆን በሲ.ፒ.አ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በራሳቸው የዋጋ ማቅረቢያ (Proforma invoice) ላይ በማዘጋጀት በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ እ.ኤ.አ. ታህሳስ 30 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ሜክሲኮ ፊሊፕስ ሕንጻ ቢሮ ቁጥር 119 ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በዕለቱ ታህሳስ 30 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት ላይ ከላይ በተጠቀሰው አድራሻ ቢሮ ቁጥር 119 ውስጥ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ፋብሪካው ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር፡- 0115-505607, 0115-505633
ሜክሲኮ አደባባይ ፊሊፕስ ሕንፃ
አዲስ አበባ
የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ
