በአፈ/ከሳሽ ኪዳኔ ማርያም ገሰሰና ልጆች ኃ/የተወሰነ የግል ማህበር እና በአፈ/ተከሳሽ፡- አቶ ሳሙኤል ብርሃኔ መካከል ስላለው የአፈጻጸም ክስ ክርክር በአፈ/ከሳሽ እና በአፈ/ተከሳሽ መካከል የተቋቋመው ኤልሮኢ እሽሙር ማህበር ውስጥ የሚገኙ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች ስለሚሸጡ ለመግዛት ፍላጎት ያላቸው ሰዎች እንድትወዳደሩ የኮምቦልቻ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ያሳውቃል።
የኮምቦልቻ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በአፈ/ከሳሽ፡- ኪዳኔ ማርያም ገሰሰና ልጆች ኃ/የተወሰነ የግል ማህበር እና በአፈ/ተከሳሽ፡- አቶ ሳሙኤል ብርሃኔ መካከል ስላለው የአፈጻጸም ክስ ክርክር በአፈ/ከሳሽ እና በአፈ/ተከሳሽ መካከል የተቋቋመው ኤልሮኢ እሽሙር ማህበር ውስጥ የሚገኙ፣
1ኛ የእንጨት መቀቀያ ማሽን 4 ሜትር በ26 ሜትር ላይ ያረፈ፣
2ኛ የኮምፕረሰር ማስቀመጫ እና የኤሌክትሪክ ሲስተም፣
3ኛ ማሽኑ ያረፈበት ሸድ በብረት ኤጋ ቆርቆሮ የተሰራ ግድግዳው የብረት የሆነው፣
4ኛ የማሽን ክዳን ብዛት 4 /አራት/፣
5ኛ የማሽን ድናሞ ብዛት 2 /ሁለት/፣
6ኛ የጋራ ብረት ብዛት 13 /አስራ ሶስት/፣
7ኛ የተቀበረ ግራና ቀኝ ሀዲድ 8 (ስምንት) ሜትር፣
8ኛ የታሸገ ኮንቲነር 1 (አንድ) ያልተከፈተ፣
9ኛ ኮንቲነር ብዛት 7 (ሰባት) የተከፈተ በውስጡ የተለያዩ ማሽኖች የያዘ፣ በመነሻ ዋጋ ብር 16,427,315 (አስራ ስድስት ሚሊዮን አራት መቶ ሀያ ሰባት ሺህ ሶስት መቶ አስራ አምስት ብር) በጨረታ እንዲሸጥ የጨረታ ማስታወቂ የዝግጅት ክፍሉ እንዲያወጣ፡፡ እነዚህ ንብረቶች የሚገኙት በአማራ ክልል ደ/ወሎ ዞን ኮምቦልቻ ሪጆፖሊታን ከተማ አስተዳደር ቦርከና ክ/ከተማ አየር ማረፊያ ቀበሌ እንደሆነ በጨረታው ላይ እንዲገለፅ፡፡ ጨረታው የሚካሄድበት ሰዓት ከጠዋቱ በ3፡00 እስከ 6፡30 ሰዓት በአማራ ክልል ደ/ወሎ ዞን ኮምቦልቻ ሪጆፖሊታን ከተማ አስተዳደር ቦርከና ክፍለ ከተማ አየር ማረፊያ ቀበሌ ንብረቱ በሚገኝበት ግቢ ውስጥ ሲሆን የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘቡን ተጫራቾች 2% (ሁለት በመቶ) የጨረታ መነሻውን በሲፒኦ (CPO) ሲያስይዙ፣ ሲፒኦውን በኮምቦልቻ ከተማ ወረዳ ፍ/ቤት ስም ሲያስይዙ እና ሲፒአውን ዋናውን (ኦርጅናሉን) ሲያዝይዙ ተጫራቾች በጨረታው ይሳተፋሉ፣ በማለት የዝግጅት ክፍሉ ማስታወቂያው እንዲወጣ ፍ/ቤቱ አዟል። ጨረታው በአየር ላይ የሚውለው ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ቀናት የሚቆይ መሆኑን እንገልፃለን።
የኮምቦልቻ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት
