በደ/ም/ኢ/ክ/መ/ በምዕራብ ኦሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት የዞኑ አስተዳደር ፅ/ቤት ሊያሰራ ላሰበው በሎት-1 ዋና አስተዳደር የመግቢያ በር እና አጥር ግንባታ ስራ በብሔራዊ በግልጽ ጨረታ በማውጣት ለተጫራቾች ጥሪ ማድረግ ይፈልጋል፡፡
በደ/ም/ኢ/ክ/መ/ የምዕራብ ኦሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
አስቸኳይ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
በደ/ም/ኢ/ክ/መ/ በምዕራብ ኦሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት የዞኑ አስተዳደር ፅ/ቤት ሊያሰራ ላሰበው በሎት-1 ዋና አስተዳደር የመግቢያ በር እና አጥር ግንባታ ስራ በብሔራዊ በግልጽ ጨረታ በማውጣት ለተጫራቾች ጥሪ ማድረግ ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሠረት እንደሚከተለው መስፈርቶችን አስቀምጧል፡፡ የግንባታ ስራ መስራት የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተቀመጡትን የመወዳደርያ መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡
- በኮንስራከሽን በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፊቃድ ያላቸውና ደረጀ 4 እና ከዛ በላይ የሆኑ፡፡
- ተጫራቾች ሰነድ ለመግዛትና ለማስገባት በሚመጡበት ጊዜ ለበጀት ዓመቱ የሚያገለግል የንግድ ፈቃድ የምዝገባ የምስክር ወረቀት የቫት ተመዝጋቢ ሰርቴፊኬት የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር የምስክር ወረቀት ዋናውን በማቅረብ የምዕራብ ኦሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የጨረታ ኮሚቴ ቢሮ ቁጥር 07 የጨረታውን ሠነድ የማይመለስ 900 /ዘጠኝ መቶ ብር ብቻ/ ዞን ገቢዎች በመክፈል ከመምሪያው የግዥና ንብረት አስ/ር ዋና የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 07 የጨረታውን ሠነድን በመውሰድ መወዳደር ይጠበቅባቸዋል፡፡
- በአቅራቢነት የምስክር ወረቀት እና ከግብር ነፃ መሆኑን የሚገልፅ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ለአንዱ ሎት 1 ብር 600,000/ ስድስት መቶ ሺህ ብር ብቻ/ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ የሚችል፤
- ተጫራቾች የገዙትን ሠነድ (ፋይናንሻል እና ቴክኒካል) ከላይ የተዘረዘሩትን አስፈላጊ የሆኑትን መረጃዎች ለእያንዳንዳቸው 1 (አንድ) ኦርጅናልና 2 (ሁለት) ኮፒ በማድረግ በሰም በታሸገ ፖስታ በማቅረብ (ፋይናንሻል እና ቴክኒካል) ዶክመንት በጥቅሉ በአንድ ፖስታ መታሸግ አለባቸው፡፡
- እያንድንዱ ፖስታ ላይ ማህተም መምታት እና መፈረም አለበት፡፡
- ተጫራቾች በሁሉም የዋጋ ማቅረቢያ ሠነዶች ላይ ተጫራቾች ህጋዊ ወኪል ፈርማ እና እንዲሁም የድርጀቱ ማህተም መኖር አለበት፡፡
- እያንዳንዱ ፖስታ የሚወዳደሩበት የስራ ቦታ፤ የሎት ቁጥር የተቋራጩ አድራሻ እና የተወካዩ ስልክ ቁጥር በመግልጽ መጻፍ አለበት፡፡
- ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ማንኛውም ተጫራች ቢሮ ቁጥር 07 በመሄድ የጨረታ ሰነዱን መውሰድ አለበት፡፡
- ጨረታው የሚታሸገው ጨረታው በማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን ላይ ሲሆን በነዚህ ቀናት ውስጥ በአል ወይም የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚውል ሆኖ በምዕራብ ኦሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የጨረታ ኮሚቴ ቢሮ ቁጥር 07 ከጠዋቱ 4፡00 (አራት) ሰዓት ተጫራቾች ወይም ተወካዮቻቸው በተገኙበት ይታሸጋል፡፡
ማሳሰቢያ:- መምሪያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 0967104693/0928664527
አድራሻ፡- በደ/ም/ኢ/ክ/መ/ በምዕራብ ኦሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
በደ/ም/ኢ/ክ/መ/ የምዕራብ ኦሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ
ጀሙ
