በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽህፈት ቤት በ2018 በጀት አመት በኮዋሽ ፕሮጀክት በወረዳው ውስጥ የሚገኙ በእስኩት ቀበሌ አስኩት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ት/ቤት የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ክፍል እና የቆሻሻ ማቃጠያ ክፍል ያለው ግንባታ እና የወርኮ ቀበሌ ወርኮ ጤና ኬላ ባለ ሁለት መቀመጫ ያለው መጸዳጃ ቤት፣ የእንግዴ ልጅ ማስወገጃ የለው እና የቆሻሻ ማቀጠያ ያለው ለማስገንባት ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ መለያ ቁጥር ጌ/ወ/ፋ/ግ/ጨ/መ/ቁ/06/2018
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽህፈት ቤት በ2018 በጀት አመት በኮዋሽ ፕሮጀክት በወረዳው ውስጥ የሚገኙ በእስኩት ቀበሌ አስኩት የመጀመሪያ ደረጃ ት/ት/ቤት የሴቶች ንጽህና መጠበቂያ ክፍል እና የቆሻሻ ማቃጠያ ክፍል ያለው ግንባታ እና የወርኮ ቀበሌ ወርኮ ጤና ኬላ ባለ ሁለት መቀመጫ ያለው መጸዳጃ ቤት፣ የእንግዴ ልጅ ማስወገጃ የለው እና የቆሻሻ ማቀጠያ ያለው ለማስገንባት ተጫራቾችን አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርት በሙሉ የምታሟሉ ማንኛውም ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ ሲሆን፣
- የጨረታ መወዳደሪያ ሃሳብ አቅራቢዎች የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር በጣት አሻራ ላይ የተመሰረተ እና የተረጋገጠ መረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የቫት ተመዝጋቢ የሆናችሁ፡፡
- ተቋራጭ በግንባታ ስራ ተቋራጭ በደረጃ 5BC/GC እና ከዛ በላይ የሆኑና የዘመኑን ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡ መሆኑን የሚያረጋግጥ የተሰጠ ማስረጃና የዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ አለባቸው።
- በጨረታው ለመወዳደር የሚፈልጉ ተቋራጮች የሚገዙትን የጨረታ ሰነድ ጠቅሰው በማመልከቻ ሲጠይቁ ተወካዮች ከሆኑ ከድርጅቱ ህጋዊ ውክልና ይዘው መቅረብ አለባቸው።
- ተቋራጮች የብቃት ማረጋገጫ የ2018 የታደሰ የበጀት ዓመቱ ማቅረብ የምትችሉ መሆን አለባቸው።
- ተቋራጮች በግንባታ ስራ በአቅራቢነት በኦን ላየን ብቻ የተመዘገቡ እና ስለ መመዝገባቸው የሚገልጽ መረጃ ሰርተፊኬት e-GP /Electeronic Governmente procuremente ማቅረብ ይኖርባችኋል።
- የ2018 በጀት አመት ከግብር ነጻ መሆናቸውን የሚገልጽ ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉ (Tax Clearance for 2018 E.C)
- ጨረታውን ለማዛባት የሚሞክሩ ተጫራቾች ከጨረታ ውጭ እንደ ሚሆኑ፣ ለወደፊትም በመንግስት ግዥ እንዳይሳተፉ በማድረግ የጨረታ ማስከበሪያ ውርስ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ በግልጽ ጽሁፍ የተጠየቀውን መረጃ ብቻ በአግባቡ የሚያቀርቡ እና ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ የሌለው መሆን አለበት፣ ስርዝ ቢፈጠር በተፈጠረው ቦታ ፈርማ የማኖር ግደታ መሆኑን መረዳት ይጠበቃል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታው ቴክኒካል እና ፋይናንሻል ዶክመት ሲያቀርቡ፡-
ሀ. ለቴክኒካል ዶከመንት አንድ ኦሪጅናል እና ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒዎች እያንዳንዳቸው በጥንቃቄ በታሸገ ሁሉንም በአንድ ትልቅ እናት ፖስታ በማሸግ ቴክኒካል በሚል በመለየት በድርጅቱ ባለስልጣን ተፈርሞበት እና ማህተም የተደረገበት መሆን አለበት፡፡
ለ. ለፋይናንሻል ዶክመንት አንድ አሪጅናል እና ሁለት ፎቶ ግራፊክ ኮፒዎች እያንዳንዳቸው በጥንቃቄ በታሸገ በድርጅቱ ባለስልጣን በእያንዳንዱ ገጽ የተፈረመበት እና ማህተም የተደረገበት ሆኖ ሁሉንም በአንድ ትልቅ እናት ፖስታ በማሸግ (ፋይናንሻል በሚል በመለየት እሰከ 25ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ ጌታ ወረዳ ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 06 በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ተቋራጮች የግንባታ ስራው የሚሰራበት ቦታ በአካል በማየት ስለ ማየታቸው ከት/ት/ቤቶቹና የጤና ኬላው ከዛራ ቀበሌ ዛራ ጽ/ቤት/ጤና ኬላ የተወከለ አካል የተፈረመበት እና ማተህም የተደረገበት መረጃ በመቀበል በቴክኒካል ሰነዱ መጨመር ግዴታ ይሆናል ይህንን የቦታ ምልከታ ያላያያዘ ተጫራች ከጨረታው ውጪ ይደረጋል፡፡
- ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሸያ ማድረግ ወይንም ከጨረታ እራስን ማግለል አይቻልም፡፡
- ተቋራጮች የጨረታ ማስከበሪያ ለት/ቤቶቹ እያንዳንዳቸው 10,000 (አስር ሺህ ብር) እና ለጤና ኬላው 10,000 /አስር ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPO (በካሽ) ወይም ከመድን ድርጅቶች የሚቀርብ ዋስትና በቅድመ ሁኔታ ላይ ያልተመሰረት ለ90 ቀናት ጸንቶ የሚቆይ ቦንድ በጌታ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ስም በማሰራት ከኦሪጅናል ቴክኒካል ዶክመንት ጋር በማድረግ ሁሉንም በአንድ ትልቅ እናት ፖስታ በማሸግ ቴክኒካል በሚል በመለየት በድርጅቱ ባለስልጣን ተፈርሞበት እና ማህተም የተደረገበት መሆን አለበት፡፡
- ግዥ ፈጻሚ አካል አሸናፊ ከተለየ በኋላ በሚገዛቸው የግንባታ ስራዎች 20% ፐርሰንት የመቀነስ ወይም የመጨመር መብት ይኖረዋል፡፡
- ተቋራጮች በጨረታው ሰነድ ላይ ማብራሪያ ወይም ማሻሻያ ጥያቄ ለግዥ ፈጻሚ አካል ማቅረብ የሚችሉት ጨረተው ከመክፈቻ 5 ቀናት በፊት በጽሁፍ መሆን አለበት፡፡
- በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች በግንባታ የስራ ዝርዝር የያዘ ሰነድ ጨረታው ከታወጀበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በተከታታይ እስከ 25ኛው ቀን 6፡00 ሰዓት ድረስ የጌታ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06 በመምጣት ማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይቻላል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ 25 /ሃያ አምስተኛ/ ቀን በዓል ወይም ቅዳሜ እሁድ ከሆነ በሚቀጥለው ቀን 8፡00 ሰአት በጨረታው ኮሚቴ ታሽጎ በዛው እለት 8፡30 ተጫራቾች /ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል /ባይገኙም ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ፡-
- ግዢ ፈጻሚው አካል ጨረታው በሙሉም (በከፊል) የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ይሆናል፡፡
- በአፈጻጸም ምክንያት ከዚህ በፊት በወረዳው ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ተቋራጮች መወዳደር አይችሉም።
- ማንኛውም ተጫራች ለቴክኒካል ዶክመንት የተጠየቀውን መረጃ ብቻ ግልጽ እና በማያሻማ መልኩ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል፡፡
- ተቋራጮች ት/ቤቱ ወይም ጤና ኬላው እንጂ ሁለቱም ጨረታዎች መውሰድ አይቻልም፡፡
- የቫት 7.5% የምንቆርጥ መሆኑን እናሳስባለን፡፡
- ተጫራቾች ዋጋ ስትሞሉ ቫትን ባካተተ ሁኔታ መሙላት ይጠበቅባችኋል፣ ካልሆነ ቫት እንደ ተካተተ ተቆጥሮ ይወሰዳል፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ ስልክ ቁጥር/0961178110/0967441304/0925838193 መደወል ይችላሉ፡፡
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን የጌታ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
