የቴፒ አጠቃላይ ሆስፒታል በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውሉ የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎች እና የላብራቶሪ ሬጄንት፣ የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎችና መለዋወጫዎች፣ ጄነሬተር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የቴፒ አጠቃላይ ሆስፒታል
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ
የጨረታ ማስታወቂያ
የቴፒ አጠቃላይ ሆስፒታል በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውሉ የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎች እና የላብራቶሪ ሬጄንት፣ የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎችና መለዋወጫዎች፣ ጄነሬተር በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት የጨረታ መስፈርቱን የሚያሟሉ፤
- በአከፋፋይነት/በችርቻሮ የዘመኑን ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለውና የ2018 ዓ.ም የመንግሥት ግብር የከፈለ መረጃ ማቅረብ የሚችል፤
- TIN Number ያለውና VAT ተመዝጋቢ የሆነ፤
- ለጨረታ ማስከበሪያ ብር 5,000 /CPO/ ማቅረብ የሚችል
- የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያለው፤
- ንብረቶችን እስከቦታው ድረስ ማቅረብ የሚችል
- የውል ማስከበሪያ 10% ማሲያዝ የሚችል
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ሁሉንም ሰነድ የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ከቴፒ አጠቃላይ ሆስፒታል ግ/ክ/የሥራ ሂደት መግዛት ይቻላል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒውን በፖስታ በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት በ15ኛው ቀን በ10፡00 ተዘግቶ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ቴፒ አጠቃላይ ሆስፒታል ግ/ክ/የሥራ ሂደት በይፋ ይከፈታል ዕለቱ በዓል /ዝግ/ ከሆነ በቀጣይ የሥራ ቀን ጨረታው ይከፈታል፤
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ /በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በደ/ም/ኢ/ሕ/መንግሥት በሸካ ዞን የቴፒ አጠቃላይ ሆስፒታል
