የአፈፃፀም ከሳሽ ስንቄ ባንክ መልካ ሶዳ ቅርንጫፍ የአፈፃፀም ተከሳሽ 1ኛ ሰለሞን አዶላ እና ታምራት ማህበር 2ኛ መልካ ሶዳ ወረዳ አስተዳደር መካከል ያለውን ክርክር አስመልክቶ ምዕራብ ጉጂ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የስሌዳ ቁጥር ኦሮ 4582 የሆነ ንብረትነቱ የነኛ የአፈፃፀም ተከሳሽ ሰለሞን አዶላ እና ታምራት ማህበር የሆነ ትራክተር የሚሸጥ ስለሆነ በዚህ ጨረታ ላይ እንድትወዳደሩ ይጋብዛል።
በምዕራብ ጉጂ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የፍትሐብሄር ጉዳዮች ችሎት
1ኛ የጨረታ ማስታወቂያ
የአፈፃፀም ከሳሽ ስንቄ ባንክ መልካ ሶዳ ቅርንጫፍ የአፈፃፀም ተከሳሽ 1ኛ ሰለሞን አዶላ እና ታምራት ማህበር 2ኛ መልካ ሶዳ ወረዳ አስተዳደር መካከል ያለውን ክርክር አስመልክቶ ምዕራብ ጉጂ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የስሌዳ ቁጥር ኦሮ 4582 የሆነ ንብረትነቱ የነኛ የአፈፃፀም ተከሳሽ ሰለሞን አዶላ እና ታምራት ማህበር የሆነ የእዳ አፈፃፀም ውሳኔ ጠቅላላ ብር 5,093,137.52 (አምስት ሚሊዮን ዘጠና ሶስት ሺ አንድ መቶ ሰላሳ ሰባት ብር ከሀምሳ ሁለት ሳንቲም) ከሳሽ ስለጠየቅ የሚሸጥ ስለሆነ ከዚህ በላይ የተገለፀው ትራክተር መነሻ ዋጋ ብር 4,781,374.05 /አራት ሚሊዮን ሰባት መቶ ሰማንያ አንድ ሺህ ሶስት መቶ ሳባ አራት ብር ከ 05 ሳንቲም/ በመያዝ 1ኛ ጨረታ በሚታይ ቦታ በመለጠፍ ከቀን 06/04/2018 ዓ.ም እስከ ቀን 20/04/2018 ዓ.ም አስራ አምስት ቀን ከቆየ በኋላ በቀን 24/04/2018 ዓ.ም ትራክተሩ ወደ ሚገኘበት ቦታ ታዛቢዎች ባሉበት ጠዋት 5፡00-8፡00 መካከል ጨረታ በመክፈት ከተወዳዳሪዎች ከፍተኛ ዋጋ ላቀረበ ሽያጩን ማካሄድ ይፈልጋል።
ስለዚህ በዚህ:-
ጨረታ ማንኛውም መሳተፍ የሚፈልግ በተባለው ቀን እና ሰዓት በመገኘት መሳተፍ እንድትችሉ ጨረታውን ያሸነፈው አካል ከጠቅላላ ክፍያ 25% ወዲያውኑ የሚከፍል ሲሆን ሙሉ ክፍያ ጨረታ ከተፈጸመ ቀን ጀምሮ በ15 የስራ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ የጨረታው አሸናፊ መብቱን በማጣት አዲስ ጨረታ ድጋሚ የሚወጣ መሆኑን ተረድታችሁ ተወዳዳሪዎች ጨረታ ላይ የተጋበዛችሁ መሆኑን እናሳውቃለን።
በምዕራብ ጉጂ ዞን ከፍተኛ የፍትሐብሔር ችሎት
