Tender Detail

Tender Details

  • Company በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ (Sidama National Regional Government Livestock Development Office)
  • Address ሀዋሳ ከተማ ጎርጋዳ ሰፈር ከፍ ብሎ ሲዳማ ብ/ክ/መ እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ሕንፃ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 16 ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0916108360
  • Website
  • Deadline05 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Securityለቆርቆሮና ሚስማር ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) እና ለሐር ልማት ቁሳቁስ 20,000 (ሃያ ሺህ ብር)
  • opening date2026-01-05 00:00:00
  • Categories Building Materials , Agricultural Materials , Machinery And Vehicles , Construction Materials And Raw Materials

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት የሐር ልማት ቁሳቁስ (ለ3ኛ ጊዜ) እና ለዶሮ ቤት መስሪያ የሚያስፈልግ የግንባታ ዕቃ/ቆርቆሮና ሚስማር /ህጋዊ ተጫራቾችን በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ (Sidama National Regional Government Livestock Development Office)


 

የጨረታ ማስታወቂያ መለያ ቁጥር 05/2018 ዓ.ም

 

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት የሐር ልማት ቁሳቁስ (ለ3ኛ ጊዜ) እና ለዶሮ ቤት መስሪያ የሚያስፈልግ የግንባታ ዕቃ/ቆርቆሮና ሚስማር /ህጋዊ ተጫራቾችን በሀገር አቀፍ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት ተጫራቾች ማሟላት የሚገባቸው መስፈርቶች፡-

  1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ፣ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆነ፣ በጨረታ መሳተፊ የሚችልና የምዝገባ ምስክር ወርቀት ማቅረብ የሚችል/ የሚትችል።
  2. ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 (አስራ አምስት ቀን) ተከታታይ ቀናት የጨረታ ዶክመንት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ) ባንክ በማስገባት ከመ/ቤቱ ግዥ ኬዝ ቲም ከጎርጋዳ ሰፈር ከፊ ብሎ ሲዳማ ብ/ክ/መ/እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ሕንፃ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 16 በአካል ሆነ በተወካዮቻቸው አማካይነት መግዛት ይቻላል።
  3. የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) ለቆርቆሮና ሚስማር ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ ብር) እና ለሐር ልማት ቁሳቁስ 20,000 (ሃያ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና /Bank GAURANT/ ወይም የክፍያ ማዣያ (CPO) ከ መጨረ ቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ።

የ ጨረታ ማስከበሪያ ከቴክኒካል ሰነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት ።

  1. አሸናፊ ሆኖ የሚመረጠው ተጫራች የውል ማስከበሪያ የሚሆን ገንዘብ በሲፒኦ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ያሸነፈበት ጠቅላላ ዋጋ 10% ማስያዝ አለበት።
  2. ተጫራቾች በገዙት ሰነድ መሰረት ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴከኒካል አንድ ዋና (ኦርጅናል)እና ሁለት ኮፒዎችን ሰነድ በተለያየ ፖስታ በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተውና በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመፃፍ ህጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን (ተከታታይ ቀናት) ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ግዥ ኬዝ ቲም ለዚሁ አገልግሎት በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል። በአስራ ስድስተኛው ቀን ሰነድ መሸጥና መግዛት አይቻልም።
  3. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወከሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8፡00 ላይ ይከፈታል። የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም።
  4. መ/ቤቱ የተሻለ ዜደ ካገኝ ጨረታውን በከፊል ሆነ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው።
  5. መ/ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ የድርጅት ህጋዊ ማህተም ሳያደርግ የቀረበ ተጫራች ከውድድሩ ውጪ ይሆናል።
  6. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል።
  7. የሰነድ ማስገቢያ ከመጨረሻው ቀንና ሰዓት በኋላ የሚመጡ አመልካቾች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
  8. በተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 0916108360/0916070057 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

 

አድራሻ:- ከጎርጋዳ ሰፈር ከፊ ብሎ በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ ህንፃ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 16 እንገኛለን።

 

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት እንስሳት ሀብት ልማት ቢሮ

ሀዋሳ

 

Save Tender