Tender Detail

Tender Details

  • Deadline09 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Security70,000 /ሰባ ሺህ ብር/
  • opening date2026-01-09 00:00:00
  • Categories Construction Works , Contractors

በአብክመ በከሚሴ ከተማ አስተዳደር የከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በክልል ልዩ ድማ በጀት በ05 ቀበሌ ለሚሰራው 394 ሜትር የውሃ ተፋሰስ ቦይ ግንባታ ሥራ ለማስገንባት ድርጅቶች ተቋራጮች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

 

በአብክመ በከሚሴ ከተማ አስተዳደር የከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በክልል ልዩ ድማ በጀት በ05 ቀበሌ ለሚሰራው 394 ሜትር የውሃ ተፋሰስ ቦይ ግንባታ ሥራ ለማስገንባት ድርጅቶች ተቋራጮች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች /ድርጅቶች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

  1. ደረጃቸው GC/ 7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ፣
  2. ለሥራው ሕጋዊ አግባብነት ያለው ፈቃድ ኖሯቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና እድሳት ያደረጉ፣ ለሥራው የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፣ የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN ያላቸው።
  3. የጨረታው ሰነድ ከከሚሴ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 በግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ዋና የሥራ ሂደት ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ 21 ተከታታይ ቀናት ከላይ የተዘረዘሩትን መረጃዎች ዋናና ኮፒ በመያዝ ዘውትር በሥራ ቀንና ሰዓት ለእያንዳንዱ ሰነድ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታውን የፋይናንሻል ሰነድ ለየብቻው ዋና እና ኮፒ በማድረግ በታሸገ ኢንቨሎፕ በአብክመ በከሚሴ ከተማ አስተዳደር ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በግዥ ፋይ/ንብ/አስ/ዋና የሥራ ሂደት ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በሃያ ሁለተኛው ቀን /22ኛው/ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ሰዓት እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ 394 ሜትር የውሃ ተፋሰስ ቦይ ግንባታ ሥራ የጨረታ ሰነድ ማስገባት ይኖርባቸዋል ።
  5. ጨረታው በቀን 1/5/2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4:30 ሰዓት በግዥ/ፋይ/ንብ/አስ/ዋና የሥራ ሂደት ቢሮ ተጫራቾች ወይንም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
  6. ተጫራቾች ተመላሽ የሚደረግ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ገንዘብ ብር 70,000 /ሰባ ሺህ ብር/ በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ ትእዛዝ /CPO/ ማስያዝ አለባቸው።
  7. የጨረታ አሸናፊ የሆነው ድርጅት ውል በሚዋዋልበት ጊዜ የውለታ ማስከበሪያ ከአጠቃላይ ድምር ዋጋ 10% ማስያዝ ይኖርበታል።
  8. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  9. በፋይናንስ ግምገማ ያለፉ ተጫራቾች በቁጥር ቢያንስ 3 እና ከዚያ በላይ ከሆኑ በጨረታ አከፋፈት ወቅት ከተነበበው አጠቃላይ ዋጋ ላይ የሂሳብ ስሌት አቲሜቲክ ቼክ ከተሰራ በኋላ የተደረሰበት ልዩነት እስከ 2.5% ድረስ ከሆነ ተቀባይነት የሚኖረው ሲሆን ከዚህ የበለጠ ልዩነት ካጋጠመ ከውድድር ውጭ ይሆናል።
  10. ከ3 በታች ከሆነ በጨረታ አከፋፈት ወቅት ከተነበበው አጠቃላይ ዋጋ ላይ የሂሳብ ስሌት አርቲሜቲክ ቼክ ከተሰራ በኋላ የተደረሰበት ልዩነት እስከ 1% ድረስ ብቻ ተቀባይነት የሚኖረው ሲሆን ከዚህ በላይ ከሆነ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
  11. የሂሳብ ስለት አርቲሜቲክ ቼክ በግዥ ፈጻሚ መ/ቤት ባለሙያ ከሚያስተካከለው ውጭ ተጫራቾች የሚቀርበው የመጫረቻ ሰነድ ላይ በነጠላ እና ጠቅላላ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ተጫራቹ ከጨረታ ውጭ ይሆናል፡፡
  12. ተጨማሪ ማብራሪያ ከፈለጉ የከሚሴ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በግንባር በመቅረብ ወይንም በስልክ ቁጥር፡- 033 554 1015/033 554 0144 ደውለው መረዳት ይችላሉ።

 

በከሚሴ ከተማ አስተዳደር የከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት

 

Save Tender