በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት በቤንች ማጂ አንድነት የገ/ሁ/ህ/ስራ ዩኒዬን በ2018 በጀት ዓመት ለአርሶ አደሩ ምርት ዘመን አገልግሎት የሚውል የተለያዩ አይነት ያላቸው የአፈር ማዳበሪያ ከቤ/ሸኮ ዞን ማእከላዊ መጋዘን በዞኑ ለሚገኙ ወረዳዎችና በሸካ ዞን ለሚገኙ ወረዳዎች ለማጓጓዝ ስላቀደ የተሽከርካሪ ባለንብረቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ለማሰራት ይፈልጋል።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የቤንች ማጂ አንድነት የገ/ሁ/ህ/ስራ ዩኒዬን
የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት በቤንች ማጂ አንድነት የገ/ሁ/ህ/ስራ ዩኒዬን በ2018 በጀት ዓመት ለአርሶ አደሩ ምርት ዘመን አገልግሎት የሚውል የተለያዩ አይነት ያላቸው የአፈር ማዳበሪያ ከቤ/ሸኮ ዞን ማእከላዊ መጋዘን በዞኑ ለሚገኙ ወረዳዎችና በሸካ ዞን ለሚገኙ ወረዳዎች ለማጓጓዝ ስላቀደ የተሽከርካሪ ባለንብረቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ለማሰራት ይፈልጋል። በዚህ መሰረት በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የተሰማሩበትን የስራ ዘርፍ የሚገልጽ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው።
- የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር ያላቸው።
- የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል።
- የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ከመንገድ ትራንስፖርት ማቅረብ የሚችል።
- የባለቤትነት ሊብሬ ማቅረብ የሚችል።
- የታደሰ መድን ሽፋን ወይም መድን ፈንድ ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዶች ጋር የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ CPO በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ማቅረብ የሚችል።
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ከቤ/ሸኮ ዞን የቤንች ማጂ አንድነት የገ/ሁ/ህ/ ስራ ዩኒዬን ቢሮ ቁ.2 በመቅረብ የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 500 አምስት መቶ/ በመክፈል መውሰድ ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች የገዙትን ሰነድ ፋይናሻልና ቴክኒካልን ኦሪጅናል እና ኮፒ ለየብቻው በአንድ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው።
- ተጫራቾች በሁሉም የዋጋ ማቅረቢያ ሰነዶች ላይ የተጫራቾችን ህጋዊ ውክልና፤ ፊርማ፤ የድርጅቱን ማህተም፣ ፋይናሻልና ቴክኒካል፣ ኦሪጅናልና ኮፒ በማለት ፖስታው ላይ በመጻፍ እንዲሁም አድራሻና ስልክ መግለጽ መቻል አለባቸው።
- የትራንስፖርት የመጫን አቅም 100 (አንድ መቶ ኩንታል እና ከዚያ በላይ
- ይህ ጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ጀምሮለ 15 ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን በ15ኛው በቤ/ማ/አ የገ/ሁ/ህ/ ስራ ዩኒዬን ቢሮ ከጠዋቱ 4፡00 ተጫራቾች ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ሆኖም ጨረታው የሚታሸግበትና የሚከፈትበት ከመንግስት ስራ ሰዓት ውጭ/በበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ስራ ቀን ይሆናል።
ማሳሰቢያ፡- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ/በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልላዊ መንግስት የቤንች ማጂ አንድነት የገ/ሁ/ህ/ስራ ዩኒዬን
