Tender Detail

Tender Details

  • Company በሀገር መከላከያ ሚንስቴር የሜካናይዝድ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ
  • Address , Phone: 0968408512
  • Website
  • Deadline31 Dec 2025, 12:00 AM
  • magazineAddis Zemen
  • Bid Document Price300.00
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-12-31 00:00:00
  • Categories Furniture , Electronics Materials

በሀገር መካላከያ ሚኒስቴር በሜካናይዝድ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ሥር የሚገኙ ከታች የተገለፁትን የተለያዩ ንብረቶች በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በሀገር መከላከያ ሚንስቴር የሜካናይዝድ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ


የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶች ሽያጭ

የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር A01/2018

 

በሀገር መካላከያ ሚኒስቴር በሜካናይዝድ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ሥር የሚገኙ ከታች የተገለፁትን የተለያዩ ንብረቶች በጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።

  1. የተለያዩ ያገለገሉ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣
  2. የተለያዩ ያገለገሉ የፈርኒቸር፣ ቁሳቁስ እና ተገጣጣሚ እቃዎችን፡፡

ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም በጨረታው ላይ መሳተፍ የሚፈልግ አካል በጨረታው መሳተፍ ይችላል።

  1. ዕቃዎቹ ለዕይታ ክፍት የሚሆኑት ከ10/4/2018ዓ.ም እስከ 22/4/2018 ዓ.ም ድረስ ብቻ ይሆናል።
  2. ዕቃዎቹ የሚገኙበት ቦታ (ሰመራ፣ ዲቼቶ፣ ኤሊዳር፣ ዳንሻ፣ ቀብሪ ደሃር) ሲሆኑ
  3. የጨረታ ሰነዱን ከተጫራቾች ዝርዝር መመሪያ ጋር የማይመለስ 300 ብር በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ባሉት የሥራ ቀናት ውስጥ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ በር 200 ሜትር ዝቅ ብሎ ከሚገኘው የሜካናይዝድ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ያሉበት ቦታ ዴቼቶ፣ ዳንሻ፣ ቀብሪ ደሃር መግዛት ይችላሉ።
  4. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ሰነዱ ላይ በተገለጸው የገንዘብ መጠን መሠረት ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
  5. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  6. ጨረታው ታኅሣሥ 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ተዘግቶ በዕለቱ ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሜ/ድ ዕዝ ንብረት አስተዳደር ቡድን በሚያዘጋጀው ቦታ ይከፈታል።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 68 40 85 12 ወይም 09 13 63 48 60

 

በሀገር መከላከያ ሚንስቴር የሜካናይዝድ ዕዝ ጠቅላይ መምሪያ

 

Save Tender