በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ወታደራዊ ፍትህ ዋና ዳይሬክቶሬት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የወታደራዊ ፍትህ ዋና ዳይሬክቶሬት
የመደበኛ ዕቃ ግዥ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር ወታደራዊ ፍትህ ዋና ዳይሬክቶሬት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
እነርሱም የፅዳት፣ የፅህፈት፣ የስልጠና ዕቃዎች፣ የኤሌክትሪክ ጥገና ዕቃዎች ሲሆኑ፡-
- ተጫራቾች ጨረታ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ በዘርፉ የተሰማሩበትን የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፎቶ ኮፒ አቅርበው መሆን አለበት፤
- ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈለ እንዲሁም ለተጨማሪ እሴት ታክስ መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ፣ የአቅራቢነት የድህረ ገፅ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና የቲን ሰርተፍኬት ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው የሚከናወነው በግልፅ ጨረታ ስነ-ስርዓት እና ይህንኑ አስመልክቶ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት ባወጣው የመንግስት ግዥ አዋጅ መሰረት ብቁ ለሆኑ ተጫራቾች ነው።
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00(ሁለት መቶ) በመክፈል በወታ/ፍትህ ዋና ዳይሬክቶሬት ግዥ ክፍል መከ/ዋና መ/ቤት አዲሱ ህንፃ 5ኛ ፎቅ A ብሎክ በመቅረብ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት በመግዛት ዘወትር በስራ ሰዓት የሚወዳደሩበት ዋጋ በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ ኦርጅናል እና ኮፒ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ መጠን ለፅህፈት፣ ስልጠና እና ለአልባሳት ብር 8,304.84 (ስምንት ሺ ሶስት መቶ አራት ብር ከ84/100) ለፅዳት እና ለኤሌክትሮኒክስ የጥገና ዕቃዎች ብር 15,6340 (አስራ አምስት ሺ ስድስት መቶ ሰላሳ አምስት ብር ከ40/100) ብቻ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው በ24/4/2018 ዓ.ም ከቀኑ 7፡30 ተዘግቶ በዕለቱ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወታ/ፍትህ ዋና ዳይሬክቶሬት ስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር ፡-011 318 1718
አድራሻ ፡- አዲስ አበባ ጦር ሃይሎች ሆስፒታል ፊት ለፊት በሚገኘው መከ/ዋና መ/ቤት አዲሱ ህንፃ 5ኛ A ብሎክ
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የወታደራዊ ፍትህ ዋና ዳይሬክቶሬት
