የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለቆሬ ዋር ኮሌጅ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ Supply Distribution Board, Switch and Socket” ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DCE/EM/198/2025
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ለቆሬ ዋር ኮሌጅ ፕሮጀክት አገልግሎት የሚውሉ Supply Distribution Board, Switch and Socket” ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ
|
የዕቃውን ዓይነት
|
የፕሮጀክት ስም
|
የጨረታ ቁጥር
|
የጨረታ መዝጊያ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታ መክፈቻ ቀን እና ሰዓት |
የጨረታ ማስከበሪያ
|
|
1
|
supply Distribution board, switch and socket |
ለቆሬ ዋር ኮሌጅ ግንባታ
|
DCE/ EM/198/2025
|
ታህሳስ 22/2018 ዓ.ም 4፡15 ሰዓት |
ታህሳስ 22/2018 ዓ.ም 4፡30 ሰዓት
|
100,000.00
|
ስለሆነም፡-
- ተጫራቾች በዘርፍ የተሰማሩ መሆኑን የሚገልፅ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉበት ማስረጃ፣ ለተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡበትን ግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ በጨረታ ለመሳተፍ የሚሰጥ የታደሰ የምስክር ወረቀት (ታክስ ክሊራንስ) እና የአገር ውስጥ ተጫራቾች በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆኑን የሚያረጋግጥ ኮፒ ወዘተ... ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ወይም ከታወቀ ባንክ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና (unconditional Bank Guarantee) ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በጨረታ ሰነድ በተያያዘው የስራ ዝርዝር መሠረት መሆን ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ቃሊቲ ቶታል ከአዲሱ ስታድየም ጀርባ ወይም ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ት/ቤት አጠገብ በሚገኘው የመከላከያ ኮንስትራክሽን ዋና መ/ቤት የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ መግዛት ይችላል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን የጨረታ ቴክኒካል ሰነድ እና ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው ቀንና ሰዓት በኢንተርፕራይዙ የግዥና አቅርቦት አስተዳደር መምሪያ ቢሮ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው ከላይ በሰንጠረዡ በተገለፀው መሠረት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል።
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ አድራሻ፡- ቃሊቲ ቶታል ከአዲሱ ስታድየም ጀርባ ወይም ኮማንደር አትሌት ደራርቱ ቱሉ ት/ ቤት አጠገብ
የቀጥታ ስልክ ቁጥር 011 440-3433/34
ማዞሪያ 011 442-2270/71/72
E-mail አድራሻ info@dce-et.com
የድህረ ገፅ አድራሻ www.dce-et.com
የመከላከያ ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ
