Tender Detail

Tender Details

  • Company የጋዝጊብላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ት/ቤት የግ/ን/አስ/ር ቡድን
  • Address በዋግ ኸምራ ዞን የጋዝጊቢላ ወረዳ : አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 09 20 18 32 67
  • Website
  • Deadline07 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price200.00
  • Bid Securityለሚወዳደሩበት ምድብ ከጠቅላላ ዋጋው (ቫትን ጨምሮ) 2% (ሁለት ፐርሰንት)
  • opening date2026-01-07 00:00:00
  • Categories Building Construction , Construction Works

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በዋግ ኸምራ ዞን የጋዝጊቢላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት በመደበኛ እና ከፌዴራል ትም/ት ሚኒስተር በተገኘ በጀት የጋዝጊብላ ወረዳ ትም/ት ጽ/ቤት የአበቃት ትም/ቤት የመማሪያ ክፍል እና ሽንት ቤት ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡

የጋዝጊብላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ት/ቤት የግ/ን/አስ/ር ቡድን


 

የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በዋግ ኸምራ ዞን የጋዝጊቢላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2018 የበጀት ዓመት በመደበኛ እና ከፌዴራል ትም/ት ሚኒስተር በተገኘ በጀት የጋዝጊብላ ወረዳ ትም/ት ጽ/ቤት የአበቃት ትም/ቤት የመማሪያ ክፍል እና ሽንት ቤት ግንባታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሠራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል ፡፡

  1. በሕንፃ ሥራ ተቋራጮ ንግድ ፍቃድ ያለው እና ከደረጃ 7 በላይ የሆኑ
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ነምበር) ያላቸው።
  3. የግዥው መጠን ብር 200,000 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) እና ከዛ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውንየሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ከላይ ከተራ ቁጥር ከ1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ መያዝ አለባቸው።
  5. የግንባታው አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል
  6. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የመጫረቻ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል በጋዝጊብላ ወረዳ ገ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 14 ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማግኘት ይቻላል። የጨረታ ሰነዱን በሥራ ሰአት ብቻ መግዛት ይጠበቅባቸዋል፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ (ቢድ ቦንድ) ለሚወዳደሩበት ምድብ ከጠቅላላ ዋጋው (ቫትን ጨምሮ) 2 ፐርሰንት በባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና እንዲሁም ከመ/ቤታችን ገንዘብ ያዥ በመሂ አንድ ገቢ በማድረግ ገቢ ያደረገበትን ዋናውን ደረሰኝ ኮፒ በማድረግ ኮፒውን ከጨረታ ሰነዱ ጋር በጥንቃቄ በፖስታ አሽገው ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ለሚፈልጉ በፖስታ አሽገው የጨረታ ሰነዱ ጋር ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች ይህ ጨረታ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ኮፒ በማለት እስከ 22ኛው ቀን 3፡30 ድረስ የጨረታ ሰነዱን ማስገባት የሚቻል ሲሆን በ22ኛው ቀን ከጠዋቱ 3:31 ይታሸግና በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል ይሁን እንጅ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጽ/ቤቱ ጨረታውን የመከፈት መብት አለው።
  9. የጨረታ ሰነዱ ስርዝ ድልዝ ካለዉ ወይም በፍሉድ የተሰረዘ ካለው ሰነዱ ተቀባይነት የለውም፡፡
  10. በዚህ የጨረታ ማስታወቂያ ያልተካተቱ ሕግና ደንቦች በግዥ መመሪያ ተግባራዊ ይደረጋል፡፡
  11. መ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።
  12. ተወዳዳሪዎች የሞሉት ዋጋ ከመሐንዲስ ግምቱ 25% እና ከዛ በላይ ዝቅ ብሎ ቢገባ ውለታ ከመውሰዱ በፊት አስፈላጊውን መስፈርት ማቅረብ አለበት እንዲሁም የውለታ ማስከበሪያ 25% ማስያዝ አለበት
  13. በጨረታው 1ኛ የወጣው ተጫራች ውል እስኪወስድ ድረስ 1ኛና 2ኛ የወጡ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ አይመለስላቸውም ሌሎቹ ተወዳዳሪዎች ግን አሸናፊው ከተለየ በኋላ ወዲያውኑ መውሰድ ይችላሉ።
  14. አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ከ5 የሥራቀናት በኋላ ባሉት ተከታታይ 5ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ 10 ፐርሰንት የውለታ ማስከበሪያ ይዞ በመቅረብ ውለታ መውሰድ ይኖርበታል
  15. ጨረታው በሚከፈትበት ቀን ካላንደር (ዝግ ከሆነ) በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል።
  16. በጨረታው ለመሳተፍ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በጋዝጊብላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ግ/ን/አስ/ር ቡድን ቢሮ ቁጥር 14 በአካል በመገኘት ወይም በሞባይል ስልክ ቁጥር 09 20 18 32 67 ወይም 09 21 19 21 27 በመደወል መረጃ ማግኘት ይችላሉ፡፡

 

የጋዝጊብላ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት ት/ቤት የግ/ን/አስ/ር ቡድን

 

Save Tender