Tender Detail

Tender Details

  • Company Sidama Region Agriculture Research Institute (የሲዳማ ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት)
  • Address ሀዋሳ ከተማ ፡ ሲዳማ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0911738584
  • Website
  • Deadline09 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price500.00
  • Bid Security120,000.00
  • opening date2026-01-09 00:00:00
  • Categories Construction Works

የሲዳማ ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት በ2018 በጀት ዓመት በወንዶ ጢቃ ንዑስ የምርምር ጣቢያ ግቢ ውስጥ ሊያሰራ ላቀደው የቲሹ ካልቸር ላቦራቶሪ ፣ የቢሮ ፣ የመጋዘን ፤ የጥበቃ ቤት እና የሽንት ቤት ቀሪ ግንባታ ሥራ ሕጋዊ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል።

Sidama Region Agriculture Research Institute (የሲዳማ ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት)


የጨረታ ማስታወቂያ

የሲዳማ ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት በ2018 በጀት ዓመት በወንዶ ጢቃ ንዑስ የምርምር ጣቢያ ግቢ ውስጥ ሊያሰራ ላቀደው የቲሹ ካልቸር ላቦራቶሪ ፣ የቢሮ ፣ የመጋዘን ፤ የጥበቃ ቤት እና የሽንት ቤት ቀሪ ግንባታ ሥራ ሕጋዊ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል። በዚሁ መሠረት፤

1. ደረጃቸው GC-5/BC-5 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የሥራ ተቋራጮች 2018 ዓ/ም ፈቃዳቸውን ያሳደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No.) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን ወይም ከሲዳማ ብሔራዊ ከልላዊ መንግሥት ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡

2. አስፈላጊውን የግንባታ ማቴሪያሎች፣የሥራ መሣሪያዎች እና ሌሎች ሀብቶችን በግላቸው አቅርበው ግንባታውን መሥራትና ማጠናቀቅ የሚችሉ።

3. በሲዳማ ክልል ውስጥ ሶስት (3) እና ከዚያ በላይ ፕሮጀከቶችን ውል ገብተው ግንባታ እያከናወኑ ያሉ እና ያላስረከቡ ሥራ ተቋራጮች ይህን የጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም።

4. በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ ፕሮጀከቶችን ሠርቶ ለማስረከብ ከአሠሪ እና ከሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር ሕጋዊ ውል ገብተው በሥራ ወቅት ከአሠሪ መስሪያ ቤት ወይም ከአማካሪ መስሪያ ቤት ማንኛውም ዓይነት የሥራ አፈፃፀም ማስጠንቀቂያ ተሰጥቷቸው ወደ ሥራ ገብተው ያላስተካከሉ ሥራ ተቋራጮች የጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም።

5. የሥራ ተቋራጮች ለውድድር ያቀረቡትን ብቃት (ቴክኒክ) መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና (ኦርጅናል) ሲጠየቁ አቅርበው ማመሳከር አለባቸው፤ ይህ ተጣርቶ ኮፒው ከዋናው ጋር ተመሳከሮ ትክከለኛ ካልሆነ ተቋራጩ ከውድድር ውጭይሆናል።

6. የጨረታ ማስከበሪያ (Bid security) ብር 120,000.00 (አንድ መቶ ሃያ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና /BANK GAURANTEE/ ወይም የክፍያ ማዘዣ (CPO) ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ከዚህ ውጭ በኢንሹራንስ ወይም በሌላ መልኩ የሚቀርብ የጨረታ ማስከበሪያ ተቀባይነት የለውም።

7. የሥራ ተቋራጮች በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ሕጋዊ ፊቃዳቸውንና ተዕታ (VAT) የተመዘገቡበትን ስርተፍኬትና ታክስ ከሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ዶከመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ25 (ሃያ አምስት) ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በሲዳማ ክልል ግብርና ምርምርኢንስቲትዩት ፋይናንስ ከፍል በመከፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ።

8. የሥራ ተቋራጮች ከጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት የግንባታ ሳይት በራሳቸው ወጪ አይተው ማረጋገጥ አለባቸው።

9. የጨረታው ሰንድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ የጨረታ ማስከበሪያ (Bid bond/security) ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን እንዲሁም ቴከኒካል እንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ኮፒዎችን ሰነድ በተለያየ ኢንቨሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፖስታ ውስጥ ተከተውና በሁሉም ዶከመንት ላይ ስምና አድረሻ በመፃፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ _ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ26ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት በሲዳማ ከልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ፋይናንስ ከፍል ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።የጨረታ ማስከበሪያው ከቴከኒካል ሰነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት።

10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀንና ቦታ ከቀኑ 6፡00 ላይተዘግቶ ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፣ የተጫራቶች አለመገኘት የጨረታውን መከፈት አያግደውም።

11. አሠሪው መ/ቤት የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

12. አሸናፈው ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው መሠረት ለቅድመ ከፍያ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንከ ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል።

13. የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል።

የሲዳማ ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት

ሀዋሳ ከተማ

Save Tender