Tender Detail

Tender Details


ሰርጢ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና የመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በወረዳ 08 ት/ጽ/ቤት ስር የሚገኝ የመንግስት ት/ቤት ሲሆን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ እቃዎችን በሁለተኛ ዙር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል።

ስርጢ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት


የሁለተኛ ዙር የጨረታ ማስታወቂያ

የሰርጢ ቅድመ አንደኛ/የመጀ/ደ/ት/ቤት ስ/ቁጥር 002/2018

ሰርጢ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና የመካከለኛ ደረጃ ት/ቤት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በወረዳ 08 ት/ጽ/ቤት ስር የሚገኝ የመንግስት ት/ቤት ሲሆን ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ እቃዎችን በሁለተኛ ዙር በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል።የሚያስፈልጉ ግዥዎች-የደንብ ልብስ፣ አላቂ የቢሮ እቃዎች፣ አላቂ የህክምና እቃዎች፣ ሕትመቶች፣ አላቂ የትምህርት እቃዎች፣ ቋሚ እቃዎች፣ የስፌት አገልግሎት እና የማሽነሪ ጥገና እቃዎች አወዳድሮ መግዛት/ማሰራት ይፈልጋል፡፡ሆኖም ተጫራቾች በሚመለከታቸው የንግድ ዘርፍ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል።

  • የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው እና ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ
  • የግብር ከፋይ መለያ (ቲን ቁጥር)ያላቸው እና ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ።
  • የተጨማሪ እሴት ታክስ እና የንግድ ምዝገባ የምስከር ወረቀት ሁለቱንም ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ።
  • በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የድጋፍ ደብዳቤ(የገቢዎች ከሊራንስ) ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ ።
  • በግዥ ኤጀንሲ የአቅራቢነት የተመዘገቡ እና ስለመመዝገቡ ሰርተፍኬት ኮፒ ማቅረብ የሚችሉ።
  • ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በአየር ላይይቆያል፡፡
  • ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ(ታሽጎ) በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡30 በፋ/ግ/ን/አስ/ደጋፊ የሥራ ሂደት ቢሮ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት ይከፈታል።
  • ተጫራቾች ለዚሁ የተዘጋጀውን የጨረታ ዶክመንት /ሰነድ/ የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/በመከፈል በት/ቤቱ ፋ/ግ/ን/አስ/ደጋፊ የሥራ ሂደት በመቅረብ መግዛት ይቻላል።
  • ተጫራቾች የጨረታ ዋስትና ማስከበሪያ

ሎት 1- 621 የደንብ ልብስ 16,900.00/አስራ ስድስት ሺህ ዘጠኝ መቶ ብር/

ሎት 2- 6212 አላቂ የቢሮ እቃዎች 3,300.00/ ሶስት ሺህ ሶስት መቶ ብር/

ሎት 3፡- 6213 የህትመት ስራዎች 1200.00/ አንድ ሺህ ሁለት መቶ ብር/

ሎት 4፡- 6214 አለቂ የሕከምና እቃዎች 300.00/ ሶስት መቶ ብር/

ሎት 5፡- 6215 አላቂ የትምህርት እቃዎች 8,000.00/ ስምንት ሺህ ብር/

ሎት 7፡-6243 የማሽነሪዎች ጥገና 3,000/ሶስት ሺህ ብር/

ሎት 8፡-ቋሚ እቃዎች 5,500/አምስት ሺህ አምስት መቶ ብር/

  • ባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ በየሎቱ ከጨረታ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • ተጫራቾች ከላይ የተዘረዘሩትን የንግድ ሥራ መስፈርቶች እና የመወዳደሪያ የጨረታ ዶከመንታቸውን ዋናውን እና ኮፒውን በታሸገ ኢንቨሎፕ በማድረግ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል ።
  • ተጫራቾች ሰነድ ሲመልሱ ናሙና ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  • 6 ወር ለሞላው ናሙና መስሪያ ቤቱ አይጠየቅም፡፡
  • ዋጋው ሲሞላ ስርዝ ድልዝ ካለው ወይም በፍሉድ የጠፋ ከሆነ ውድቅ የሚሆን መሆኑን እንገልፃለን።
  • ጨረታውን ያሸነፉ ተጫራቾች የውል ማስከበሪያ 10% በባንክ በተመሰከረለት ሲፒኦ ማቅረብ ይጠበቅበታል።

ማሳሰቢያ፡- መስሪያ ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ።

አድራሻ፦ አቃ/ቃ/ክ/ከ/ወረዳ 08 ወደ ስርጢ ማርያም ቤ/ክርስቲያን ሲሄዱ ልዩ ስሙ ሰላሌ ሰፈር ገባ ብሎ ጨፌ ኮንዶሚኒየም አጠገብ ።

ለበለጠ መረጃ፡- 0114 71 50 53 ይደውሉ፡፡

ስርጢ ቅድመ አንደኛ፣ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት

Save Tender