በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የሞላሌ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ፅ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለሞላሌ ከተማ አስተዳደር ማለትም ሎት 1፡- የመንግስት ሰራተኞች የህፃናት ማቆያ ክፍል ግንባታ በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አውጥቶ ግንባታውን ማስገንባት ይፈልጋል፡፡
የሞላሌ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ፅ/ቤት /ሞላሌ/
የጨረታ ቁጥር ጨ/ቁ 003/2018
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በሰ/ሸዋ ዞን የሞላሌ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ፅ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ለሞላሌ ከተማ አስተዳደር ማለትም
ሎት 1፡- የመንግስት ሰራተኞች የህፃናት ማቆያ ክፍል ግንባታ በብሔራዊ ግልፅ ጨረታ አውጥቶ ግንባታውን ማስገንባት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት፡-
1. በዘርፉ የተሰማራና የዘመኑን ግብር የከፈለበትን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር/ቲን ነምበር ያላቸው
3. የግንባታው የገንዘብ መጠን ከብር 200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ/የቫት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡
4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ ከተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱት እና ሌሎች የሚመለከታቸው ን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ በማድረግ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
5. የሚገነባው የመንግስት ሠራተኞች የህፃናት ማቆያ ክፍል ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚችሉት ኮንትራክተሮች ወይም ኢንተርፕራይዞች ከደረጃ 8/ስምንት/ እና በላይ ህንፃ ሥራ ተቋራጭ /B.ር /እና ጠቅላላ ሥራ ተቋራጭIGC/ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
6. የሚገነባው የመንግስት ሰራተኞች የህፃናት ማቆያ ክፍል ግንባታ ዓይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
7. ተጨራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የግንባታውን ጠቅላላ ዋጋ አርቲሜቲክ ቼክ ከተሰራ በኃላ የሚገኘው ጠቅላላ ድምር 2% በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንኮች በሚሰጥ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ዋስትና ወይንም በባንክ የተረጋገጠ ሌተር ኦፍ ከሬዲት /CPO/ እና በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው፡፡
8. ተጫራቶች በእያንዳንዱ የግንባታ ቢል አፍ ኳንቲቲው ውስጥ የተዘረዘሩትን የግንባታ አይነቶች መካከል ከፋፍሎ መጫረት አይቻልም፡፡፡
9. ተጫራቾች በሚያቀርበ‐ት ሰነድ ላይ ስማቸውን፣ ስልከ ቁጥራቸውን፣ ፊርማቸውና አድራሻቸውን ማስፈርና የድርጅቱን ማህተም ማድረግ አለባቸው፡፡
10. በመጨራቻ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም፡፡ ካለም አንድ ሰረዝ በማድረግ ፊርማቸውን ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡
11. ማንኛውም ተጨራች የተጫረተበትን የመንግስት ሠራተኞች የህፃናት ማቆያ ከፍል ግንባታ የጨረታ ሰነድ አንድ ወጥ በሆነ አንድ ፖስታ ብቻ ማለትም አንድ ኦርጅናል በጥንቃቄ ታሽጎ በግዢና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 2 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ22 ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታውን ሰነድ ገቢ ማድረግ ይችላሉ፡፡ በዚሁ እለት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ጨረታው በይፋ ይከፈታል፡፡
12. ይህ የግንባታው ጨረታ የሚከፈትበት ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ላይ ከዋለ ጨረታው የሚከፈተው በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ሰዓት ይሆናል፡፡
13. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን መግዣ በማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ/ ብቻ በመከፈል ከሞላሌ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ፅ/ቤት ከዋና ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 2 መግዛት ይችላሉ፡፡
14. ሌሎች በጨረታ ማስታወቂያው ላይ ያልተካተቱ ወይም ያልተገለፁ ካሉ በግዢ አፈፃፀም መመሪያ እና በአዋጁ መሰረት ተፈፃሚ ይሆናል፡፡
15. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ሰበስጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-622-07-79 ደwow ደጠይቁ
የሞላሌ ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ፅ/ቤት
