Tender Detail

Tender Details


በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ሸዋ ዞን በአለም ከተማ አስተዳደር የአልማዝ በም ፖሊ ኮሌጅ የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ የ2018ዓ.ም በጀት በስሩ ላሉ ድፓርትመንቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች ግዥ መፈጸም ይፈልጋል።

የአልማዝ በም ፖሊ ኮሌጅ


የጨረታ ማስታወቂያ

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ሸዋ ዞን በአለም ከተማ አስተዳደር የአልማዝ በም ፖሊ ኮሌጅ የግዥ፣ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ቡድን መሪ የ2018ዓ.ም በጀት በስሩ ላሉ ድፓርትመንቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ እቃዎችን ማለትም፡-

1. የጽህፈት መሳሪያ

2 የመኪና መለዋወጫ እቃዎች

3 ብረታ ብረቶች፣ የተለያዩ የህንጻ መሳሪያና የተፈበረኩ ማቴሪያሎች

4. የኤሌክትሮኒከስ እቃዎች እና የተለያዩ ሞተርና ማሽኖች

5. የኮምፒውተር እቃዎች

6. የተለያዩ ህትመቶች

7. ጣውላና ተዛማጅ ነገሮች

8. የተዘጋጁ ልብሶች፣ የልብስ ስፌት እቃዎችና ብትን ጨርቃጨርቅ

9 የጽዳት እቃዎች

በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች ግዥ መፈጸም ይፈልጋል። ስለዚህ በዘርፉ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

1. በንግድ እድሳት ጊዜ ውስጥ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ እና የንግድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN NO ያላቸው እና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ ሁሉ በማድረግ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ የሚችሉ።

2. ከላይ የተዘረዘሩትን የእቃ አይነቶች በንግድ ዘርፋቸው ብቻ መሳተፍ ይችላሉ::

3. የግዥው መጠን 200,000/ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ VAT ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ። —

4. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ አድርገው ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

5. የሚገዙ እቃዎችን አይነትና ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር ብቻ/ በመከፈል ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ ቀናት እስከ 3፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ ከቢሮ ቁጥር 6 መግዛት ይቻላል።

7. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ የሞላበትን ኦርጅናል ሰነድ እና ከላይ ከ1-3 ተራ ቁጥር የተጠቀሰውን ማስረጃዎች አንድ ላይ በማያያዝ በየንግድ ዘርፋቸው በማድረግ በጥንቃቄ በታሸገ ፓስታ በግዥ ንብረት አስተዳደር የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን እስከ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው ቀን በ4፡30 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 6 ይከፈታል።

9. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለእቃው የሞሉትን ጠቅላላ ዋጋ 1% በአካባቢው ባሉ የባንክ ቅርንጫፎች /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ሕጋዊ በሆነው በኮሌጁ ደረሰኝ አስቆርጦ ማስያዝ አለባቸው።

10. የጨረታ መከፈቻ በበዓላት ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ሥራ ሰዓትና ቀን ይሆናል።

11, ጨረታ አሸናፊ ድርጅት ወይም ግለሰቡ የሚያቀርቡትን አቃዎች ወይም አገልግሎቶች እስከ መ/ቤቱ የማድረስ ግዴታ አለበት።

12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

13. ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 06 በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011 13 20 115 ወይም 011 13 20 636 በመደወል መረጃውን ማግኘት ይችላል።

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት በሰሜን ሸዋ ዞን በአለም ከተማ ከተማ አስተዳደር የአልማዝ በም ፖሊ ኮሌጅ። ማሳሰቢያ፡- ፖስታው መታሸግ ያለበት በየንግድ ዘርፋቸው ለእያንዳንዱ ብቻ መሆኑን እንገልጸለን።

የአልማዝ በም ፖሊ ኮሌጅ

Save Tender