Tender Detail

Tender Details

  • Company የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት
  • Address ቤንች ወረዳ ፡ ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0966886973
  • Website
  • Deadline06 Jan 2026, 12:00 AM
  • magazineአዲስ ዘመን
  • Bid Document Price300.00
  • Bid Security50,000.00
  • opening date2026-01-06 00:00:00
  • Categories Construction Works

የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በወረዳው ከ/ል/ኮ/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በወረዳው በደብረወርቅ ከተማ የ33ዐ ሜትር የዲች ቦይ ስራ በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት


ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት በወረዳው ከ/ል/ኮ/ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በወረዳው በደብረወርቅ ከተማ የ33ዐ ሜትር የዲች ቦይ ስራ በጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሰረት በጨረታው ላይ ለመወዳደር ለምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘረውን ዝቅተኛ መስፈረት ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፡፡

1. ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል፤

2. ደረጃ 8 (ስምንት) እና ከዚያ በላይ የሆነ ማህበር/ተቋራጭ፤

3. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤

4. የታከስ ክሊራንስ ማቅረብ የሚችል፤

5. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (ቲን ነምበር) ማቅረብ የሚችል፤

6. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነ እና ኮፒውን አያይዞ ማቅረብ የሚችል፤

7. የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል /የምትችል፤

8. ተጫራቾች ከጨረታ ሰነዶች ጋር የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንከ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡

9. የታደሰ ህጋዊ ሰውነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፡፡

10.ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ በአሃዝ እና በፊደል መግለጽ አለባቸው፡፡ በፊደል እና በአሃዝ መካከል ልዩነት ካለው በፊደል የተገለጸው ይወሰዳል፡፡

11.ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር ሶስት መቶ (300) በመከፈል ከደ/ቤ/ወ/ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10/አስር/ በአካል በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡

12.ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ፋይናንሻል አንድ(1) ኦርጅናል እና ሁለት(2) ኮፒ እንዲሁም ቴከኒካል አንድ(1) ኦርጅናል እና ሁለት(2) ኮፒ ለየብቻ በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡

13. ተጫራቾች የሚያቀርቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ ወይም ያላካተተ መሆኑን መግለጽ ይኖርባቸዋል፡፡ ያለበለዚያ ያቀረቡት ዋጋ ቫትን ያካተተ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

14.ተጫራቾች በእያንዳዱ ሰነድ ላይ ፊርማቸውን እና የድርጅታቸውን ማህተም ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡

 

15.ተጫራቾች የጨረታ ፖስታውን በደ/ቤ/ወ/ፋ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 4 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

16. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 15 የስራ ቀናት ከፍት ሆኖ በ15ኛው ቀን ከሰዓቱ 8:00 ላይ ታሽጎ በዚያው ቀን ከቀኑ 8:30 ላይ ተጫራቸቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በይፋ ይከፈታል፣ ዕለቱ በዓል ወይም ዝግ ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡ ማሳሰቢያ፡- 1. ተጫራቾች የማህበሩ አባላት ስለመሆናቸው የስም ዝርዝር ከነ ስራ ሀላፊነታቸው የሚገልጽ ከአደራጅ መ/ቤት ለደ/ቤ/ወ/ፋ/ጽ/ቤት አድራሻ የተጻፈ ደብዳቤ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

አድራሻ፡- የደ/ቤ/ወ/ፋ/ኢኮ/ል/ጽ/ቤት

ደብረወርቅ ስልክ: - 0966886973/0917503586/0929241731 በመደወል መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ፡፡

የደቡብ ቤንች ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት

Save Tender